በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ XLPE, PVC BEDDING and PVC SHEATHING እና የትራንስፎርመር ዘይት ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት በአገር ውስጥ የሚፈፀሙ በኢንዱስትሪው የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ሥር ላለው ለሞጆ ዋየርና ኬብል ማምረቻ ግብዓት የሆኑትን XLPE, PVC BEDDING and PVC SHEATHING እና ለታጠቅ ትራንስፎርመር ማምረቻ ግብዓት የሆነውን የትራንስፎርመር ዘይት ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1. ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትጫረቱ ተጋብዟችኋል።

2. በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤

3. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

5. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin) ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

6. ተጫራቾች በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስም በብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲፒኦ (CPO)፣ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት

ለሎት 1 - XLPE, PVC BEDDING and PVC SHEATHING 650,000 (ስድስት መቶ ሃምሳ ሺ ብር) እና

ሎት -2 የትራንስፎርመር ዘይት 950,000 (ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ለየብቻው ከሰነድ ጋር በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቶች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል መሙላትና በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው።

8. ተጫቾራች የሚያቀርቡት ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት።

9. ተጫራቶች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ አንደኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል ሰነዱን በሶፍት ኮፒ መግዛት ይችላሉ።

10. ተጫራቾች በገዙትና በሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፁትንሆኔታዎች በአግባቡ በመጠቀም የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ ኤንቨሎፕ አሽገው 2ኛ ፎቅ ላይ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

12. ተጫራቾች ለጨረታ ሰነዱ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዱን ለየብቻ ለይተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

13. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ይዘጋል በዚሁም ዕለት ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3ኛ ፎቅ ላይ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

14. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡

15. ጨረታው የሚፀናበት ጊዜ 60(ስልሳ) ተከታታይ ቀናት ስለሆነ ተጫራቾችም ይህንኑ አውቀው ስለመቀበላቸው በቴክኒካል ኦርጅናል ሰነዳቸው ላይ ማረጋገጥ አለባቸው።

16. ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም፡፡ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ለቡ መብራት ኃይል ከጀነራል መርከንታይል አጠገብ
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥራችን ስልክ: +251 924 955 389 +251 910 162733 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-01
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን 4፡30
  • Bid opening: 2026-06-01 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን 5፡00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethio Engineering Group Power Equipment Manufacturing Industry
  • Buyer address: ለቡ መብራት ኃይል ከጀነራል መርከንታይል አጠገብ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published: May 22, 2026
  • Posted at: 2026-05-22T08:11:39.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders