በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የፌደራል መንግሥት ሕንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ የግንባታ እቃዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ ለ 3ኛ ጊዜ አየር ላይ የዋለ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ጨ.ፌ.መ.ህ.ግ.ፕ.ጽ/ቤት 03 /2018

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የፌደራል መንግሥት ሕንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ የግንባታ እቃዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ሟሟላት ይኖርበታል።

  • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ የሚጫረቱት ዕቃዎች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (cpo) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል።
  • ተጫራቾች ከጨረታው ቀን በፊት ንብረቶቹ በአራት ኪሎ በሚገኘው የግንባታ ሳይት ላይ በሚገኙበት ቦታ ቀርበው ማየት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በአንድ ላይ በማጠቃለል አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግ የተወዳዳሪ ስምና አድራሻ በመጻፍ ማህተም ወይም ፊርማ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ሶስት መቶ (300) ብር በመክፈል ከፌዴራል መንግሥት ሕንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ግዥና ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በሥራ ሰዓት ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ግዥና ንብረት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ላይ በግዥና ንብረት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ የመክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የሕዝብ በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና በመከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት ባይገኙ የጨረታው መከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት ለተላላፈ ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ።
  • ተጫራቾች የሚፈልጉትን እቃ ብቻ መጫረት የሚችሉ ሲሆን ከመነሻ ዋጋ በታች ማቅረብ አይችሉም፡፡ ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ ተጫራቾች ጨረታውን ተሰርዞ የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል።
  • አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉትን ዕቃ በራሳቸው የማጓጓዣ ወጪ አራት ኪሎ በሚገኘው የጠቅላይ ፍርድ ቤት የሕንጻ ግንባታ ሳይት ውስጥ ከሚገኙ መጋዘኖች ወጪ በማድረግ በ5 ቀናት ውስጥ መውሰድ ይኖርበታል።
  • ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ ራሳቸውን መግለል አይችሉም።
  • የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ቦሌ መንገድ ሀንሰም ሕንጻ ላይ 5ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 502

ስልክ፡- ቁጥር፤- 011 5 58 12 28

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የፌደራል መንግሥት ሕንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-06
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-06 14:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Building Construction Project Office
  • Buyer address: ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ፊት ለፊት ዳሸን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ጎን
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: May 22, 2026
  • Posted at: 2026-05-22T08:24:53.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders