የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ የቤት ዕቃ፣ ኮንስትራክሽን፣ አልባሳት፣ ለስፔርፓርት፣ የፅዳት ዕቃ፣ ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሐራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልጽ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዘ

  • የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣
  • የቤት ማስዋቢያ፣
  • የቤት ዕቃ
  • ኮንስትራክሽን፣
  • አልባሳት፣
  • ለስፔርፓርት፣
  • የፅዳት ዕቃ፣
  • ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሐራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች 17/09/2018 ዓም ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይልፃል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች ፦

  1. በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ።
  2. ለሐራጅ ጨረታው 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤
  3. በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፣
  4. ለሐራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል፤
  5. በግልጽ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
  6. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን ዕቃ ክፍያውን በ05 ቀናት ውስጥ መፈፀም አለበት፣
  7. እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
  8. በጨረታው ያላሸነፈ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ወዲያውኑ የመለስላቸዋል፤
  9. አሳማኝ  የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
  10. ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው ዕርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤
  11. ተጫራቹ እቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ላይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፤
  12. ተጫራች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ከቀን 17/9/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የዕቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ20/9/2018ዓ.ም 3:45 ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል!
  13. የሀራጅ ጨረታው የሚካሄደው 20/09/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤

NB:- አሽናፊ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፡ ሳምፕል ላያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-28
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published: May 22, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders