የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለ2018 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ደንብ ልብስ፣ ጫማ እና የደህንነት መጠበቂያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለጸውን ለድስትሪክታችን ሰራተኞች ለ2018 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ጥቅማጥቅም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የጨረታ መለያ ቁጥር፡- ኢመአ/ድ/ዳ/መ/ጥ/ድ/ቲ 06/2018 ዓ.ም

1.ደንብ ልብስ ጫማ እና የደህንነት መጠበቂያ

  • የደንብ ልብስ ሎት፡-1
  • ጫማ ሎት፡- 2
  • የደህንነት መጠበቂያ ሎት፡-3

ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰአት የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ) ብር በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000322267979 ገቢ በማድረግ ድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ቢሮ ግዥ ከፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።

  • በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል
  • ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) ብር በባንክ ሲፒኦ ወይም ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  • ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ይዘጋል በዚሁ እለትም ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አካባቢ በሚገኘው በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት የመሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።
  • የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡-

  • በቅድመ ግምገማ ያለፉ ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙና በመ/ቤቱ ናሙና መራጭ ኮሚቴ ታይቶተቀባይነት ካገኙት መካከል በዋጋ ዝቅተኛ ሆኖ የተገኘው በአሸናፊነት ይመረጣል።
  • የሚፈለገውን የሰራተኞች ጥቅማጥቅም አይነትና ብዛት በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር መመልከት ይቻላል።
  • ዲስትሪክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

ስልክ ቁጥር፦025111-13-13 /0927636126/0919008017

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-10
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት
  • Bid opening: 2026-06-10 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Ethiopian Roads Administration Dire Dawa Road Maintenance District
  • Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: May 24, 2026
  • Posted at: 2026-05-25T07:41:30.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders