በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሥር በሚገኙ የተለያዩ የስራ ክፍሎች አገልግሎት ሠጥተው ተመላሽ የተደረጉ የቢሮ ዕቃዎች፣ የግንባታ ዕቃዎች እና ተሽከርካሪዎች ሞተርሳይክሎች እና የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሥር በሚገኙ የተለያዩ የስራ ክፍሎች አገልግሎት ሠጥተው ተመላሽ የተደረጉ የቢሮ ዕቃዎች የግንባታ ዕቃዎች እና ተሸከርካሪዎች ሞተርሳይክሎች እና የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች

1, በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ፋሲሊቲ ማናጅመንት ቢሮ ቁጥር 209 በመምጣት በርፖሬሽኑ ሥር በሚገኙ ከፍሎች አገልግሎት ሠጥተው ተመላሽ የተደረጉ የቢሮ የግንባታ የተለያዩ እቃዎችን ዝርዝር የሰራ መረጃ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ከፍለ መውሰድ ይችላሉ፡፡

2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚገዙትን ንብረቶች ብቻ የጥቅል ዋጋ እንዲሰጥ እና የንብረቱን ዋጋ 15% የተጨማሪ እሴት ታከስ በማሣየት ድምሩን በእሃዝ ያለስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ሥራ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ፋሲሊቲ ማናጅመንት ቢሮ ቁጥር 209 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው በየምድቡ ከተቀመጡት የጥቅል ዋጋ ዕቃዎች መካከል ተጫራቹ የሚያስፈልጋቸውን ዕቃዎች ብቻ መርጦ አይችልም

3. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመሥርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም

4. ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በታሸገው ኢንቨሎፕ እና በመጫረቻ ሠነዶቹ ላይ በማስፈር በፊርማ ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል!

5. ተጫራቾች ለሚገዙት ንብረት በእያንዳንዱ የስራ ክፍል ስር ለተቀመጡ የቢሮ፣ የግንባታ እና የተለያዩ እቃዎች ሊወገዱ ካቀረቡት ጥቅል የጨረታ ዋጋ ላይ 20 በመቶ (20%) በማስላት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ሣጥኑ ውስጥ አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡

6. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛ ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር ጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም

7. ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሠዓት በኃላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም፣

8. የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል!

9. የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በኮርፖሬሽኑ የውስጥ ማስታወቂያ ሠሌዳና በደብዳቤ እንዲገለጽ ይደረጋል፤

10. ተጫራቾች የጨረታው ውጤቱ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የማስታወቂያ ስሌዳ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምር ቅሬታ ካላቸው በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጽሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል

11. በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ በማቅረብ አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ 7ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይደረጋል፤

12. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ዕቃዎቹን በዐ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በወቅቱ ካላነሱ የዕቃዎቹን ጠቅላላ ዋጋ 0.001% /1/1000/ በየቀነ እየተሠላ በመቀጫነት እንዲከፍሉ ይደረጋል፤ ሆኖም የመቀጫው መጠን የጠቅላላውን ዋጋ 10% ሲደርስ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ተደርጎ አሸናፊነታቸው ይሠረዛል።

13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች 011-8-553627 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፣

14 ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡት ዋጋ ከማንኛውም ግብር (Taxes) በፊት መሆን አለበት።

15. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-08
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛ ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-08 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛ ቀን ጠዋት በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Housing Corporation
  • Bid bond: 20 በመቶ (20%)
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 24, 2026
  • Posted at: 2026-05-25T08:04:29.000Z
  • Buyer website: https://www.fhc.gov.et

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders