የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የዶሮ መኖ ግብዓት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጼጼ ዶሮ ብዜት ማዕከል የዶሮ መኖ ግብዓት አቅርቦት ግዥ ጨረታ ቁጥር 0--/2018ዓ/ም

ከላይ የተቀመጠውን ግዥ ለመፈፀም የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለ2018 ዓ/ም በዘርፉ የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ ለ2018 ዓ/ም የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ በሀገር ውስጥ ገቢዎች የጨረታ ተሳታፊነት የድጋፍ ደብዳቤ ያለውን የታደሠ የአቅራቢነት ሰርትፊኬት ያላቸውን ተወዳዳሪዎች በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1. ዝርዝር ጨረታውን የያዘ ሠነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/በመክፈል በቤ/ጉ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ በግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይቻላሉ።

2. የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3. አሸናፊ ድርጅት የውል ስምምነት ሲፈርም ለውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ያስይዛል።

4. በጨረታው ያልተመረጡ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ አሸናፊ እንደታወቀ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሠነዱን በመግዛት እስከ 16ተኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ16ኛው የስራ ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ሆኖ ነገር ግን ቅዳሜ፡እሁድ እና የህዝብ በዓል ቀን ላይ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘጋል።

7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ16ኛው የስራ ቀን ከጥዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አሶሳ በሚገኘው በቤ/ጉ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ በግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ይሆናል።

8. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- 0577752144 አሶሳ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-08
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-08 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከጥዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Beneshangul Gumuz
  • Publishing entity: Benishangul Gumuz Regional State of Agriculture Bureau
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: May 24, 2026
  • Posted at: 2026-05-25T08:17:11.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders