አዲስ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል አ.ማ. የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች ባሉበት ደረጃ በዝግ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር/001/2018

አዲስ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ ዕቃዎች ባሉበት ደረጃ በዝግ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል።

ሎት - 1 - የመጸዳጃ ቤት ዕቃዎች

ሎት - 2 - አልሙኒየም

ሎት - 3 - መስታወቶች

ሎት - 4 - ብረቶችና ኤጋ ቆርቆሮ

 ሎት - 5 - ልዩ ልዩ መብራቶች

 ሎት - 6 - ሊፍቶች

ሎት - 7 - የወለል ንጣፍ (SPC)

ሎት - 8 - የእንጨት በሮች

ሎት - 9 - መጋረጃ እና ምንጣፍ

ሎት - 10 - ፈርኒቸር

ሎት - 11 - የቢሮ ዕቃዎች

ሎት - 12 - ባህላዊ ቤት ማስዋቢያ

ሎት - 13 - ያገለገለ ተሽከርካሪ

 

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣ በኋላ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ብር 500 (አምስት መቶ) በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል አ.ማ ስም በተከፈተው አካውንት ቁጥር 1000616070839 ገቢ በማድረግ ያስገቡበትን ሰነድ በመያዝ ክጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 313 ተገኝተው ደረሰኝ መውሰድ ይችላሉ።

በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ-ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

  1. ከጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
  2. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ከሚመረትበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4) ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ በክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ /CPO/ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ኢማ ስም አሰርተው በታሸገ ኢንቬሎፕ ከነሙሉ አድራሻው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  3. ማንኛውንም ተጫራች የሚገዛውን የንብረት አይነት በመጥቀስ በኩባንያው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ሞልቶ በታሸገ ኢንቨሎፕ (ፖስታ) በማድረግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  4. የጨረታው መወዳደሪያ ሰነድ ግልፅ እና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን ይኖርበታል። ስርዝ ድልዝ የተደረገበት ዋጋ ከሆነ በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ፈራሚ አካል ፓራፍ/ኢንሺያል ፊርማ ማድረግ ይኖርበታል::
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፊደል እንዲሁም ከቫት በፊት እና በኋላ መሆኑ መገለፅ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች ንብረቶቹን ግንቦት 28 እና 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት ከ3፡00 6፡00 እና ከሰዓት ከቀኑ 7፡30 – 11፡00 በእያንዳንዱ ቀን ቀደም ብሎ ቀጠሮ በማስያዝ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ሲ ኤም ሲ አደባባይ ፀሀይ ሪል እስቴት ፊት ለፊት በሚገነኘው የኩባንያው ንብረት ክፍል ውስጥ ማየት ይቻላሉ።
  7. የጨረታ መዝጊያ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት እና መክፈቻ ቀን ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ይሆናል። ጨረታው በኩባንያው ንግድ ማዕከል ህንፃ 3ኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  8. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፈበትን ሙሉ ክፍያ በመፈፀም ያስያዘውን ሲፒኦ (CPO) መውሰድ የሚችል ሲሆን ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሊፒኦ (CPO) አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 3 (ሶስት) የስራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ይመለስላቸዋል።
  9.  አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ለኩባንያው ከፍለው ንብረቱን በ3 ቀናት ውስጥ መረከብና በራሳቸው ወጪ ማንሳት ይኖርባቸዋል።
  10. በተባለው ጊዜ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉም ሆነ ገቢ አድርገው ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ /ሲፒኦ/ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ ንብረቱ እንደ አስፈላጊነቱ ለሁለተኛ አሸናፊ ወይም በድጋሚ ሰጨረታ ይቀርባል።
  11. አሸናፊ ተጫራቾች ለተጫረቱበት ንብረት ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላሉ።
  12. ኩባንያው ስለንብረቶቹ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሽያጩን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አዲስ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ኢማ

አድራሻ፦ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ሲ ኤም ሲ አደባባይ ፀሀይ ሪል እስቴት ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 667 0082


Tender details

  • Deadline: 2026-06-12
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-06-12 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: አዲስ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል አማ
  • Bid bond: 25%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: May 24, 2026
  • Posted at: 2026-05-25T09:17:14.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders