ዮቴክ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግል ማህበር የኮንስትራክሽን ዕቃዎች፣ ያገለገሉ አርኤችኤስ፣ አዲስ ስፔር ፓርት መለዋወጫ ዕቃዎች እና አዳዲስ የቧንቧ ዕቃዎች መሸጥ ይፈልጋል

Description

 የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ዮቴክ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግል ማህበር የኮንስትራክሽን ዕቃዎች፣ ያገለገሉ አርኤችኤስ፣ አዲስ ስፔር ፓርት መለዋወጫ ዕቃዎች እና አዳዲስ የቧንቧ ዕቃዎች በሚገኙበት በ ገላን ከተማ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

  1. ተጫራቶች የሚጫረቱትን ንብረት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 8 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን ዋና ቢሮ 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል የማይመለስ ብር 300 በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቶች ንብረቱ በሚገኘው ገላን ከተማ ቀርበው መመልከት ይችላሉ።
  3. ማንኛውም በጨረታው ላይ የሚሳተፋ ተጫራቶች የተጠቀሱት ንብረቶች የጨረታው ማስከበሪያ (Bid Bond) ከምታቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 5% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ ከዋናው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቶች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ዶክመንት ዉስጥ በተዘጋጀዉ የማጫረቻ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ዉስጥ አስገብተዉ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 16/9/2018 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት ቅዳሜን ጨምሮ 8 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ ዋናዉ መ/ቤት መግቢያ ላይ ባለዉ የእንግዳ መቀበያ አጠገብ በተቀመጠዉ ሳጥን ዉስጥ  ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታዉ በቀን 25/9/2018 ዓ/ም ማክሰኞ 11፡00 ሰአት ይዘጋል።
  6. ጨረታው ተጫራቶች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅታችን ዋና መ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በቀን 26/9/2018 ዓ/ም ሮብ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይከፈታል። ተጫራቶች ወይም ወኪሎቻቸው ካልተገኙ ጨረታው በጨረታ ኮሚቴና ታዛቢ ባሉበት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
  7. ተጫራቶች የሚያቀርቡት ዋጋ ተ/እ/ታ /VAT/ ያካተተ መሆን ይኖርበታል።
  8. ተጫራቶች ያስያዙት ሲፒኦ ካቀረቡት ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ።
  9. የመጫረቻ ዋጋ ቅፅ ላይ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ እና አሻሚነት ያለው የቁጥር አፃፃፍ ተቀባይነት የለውም።
  10. የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሎት 5 ቀናት ውስጥ ክፍያውን ሙሉ በሙሉ ከፍለው ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል።
  11. የጨረታው አሸናፊዎች ክፍያ ከፈፀሙ በ10 ቀናት ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርትና ወጪ ንብረቱን ሙሉ በሙሉ ማንሳት ይኖርባቸዋል።
  12. የጨረታው አሸናፊዎች ክፍያ በተቀመጠው በ5 ቀናት የጊዜ ገደብ ካልከፈለ ጨረታው ውድቅ ሆኖ ለጨረታው ያስያዙት /bid bond/ ተመላሽ አይደረግም።
  13. በጨረታው ተሳታፊ ሆነው ጨረታውን ላላሸነፋ ተጫራቶች ለጨረታው ያስያዙት (Bid Bond) ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል።
  14. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ
አድ¬ራሻ፡– ዮቴክ ኮንስትራክሽን ኃ. የተ. የግል ማህበር
ቫቲካን ፊት ለፊት ያለው መርየም ህንፃ እንገኛለን
የስልክ ቁጥር 011 557 3196/ 011 557 3198
ፋክስ 011 557 3187/ 011 557 3197
ኢ-ሜይል yotekconplc@gmail.com 
        አዲስ አበባ

 


Tender details

  • Deadline: 2026-06-02
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-06-03 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yotek Construction P.L.C
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: May 24, 2026
  • Posted at: 2026-05-25T11:37:48.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders