አንበሳ ባንክ አ.ማ. አውቶሞቢል በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
አንበሳ ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና 216/1992 እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሰንጠረዡ ላይ የተጠቀሰውን ንብረት በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ
|
የተበዳሪ ስም |
የአስያዥ ስም |
አበዳሪ ቅርንጫፍ |
የመኪናዉ ዓይነት፣ የሰሌዳ ቁጥር፣ የሻንሲ ቁጥርና የሞተር ቁጥር |
የመነሻ ዋጋ |
የጨረታ ቀን
|
||||
|
የሰሌዳ ቁጥር |
የመኪና ዓይነት |
የሞተር ቁጥር |
የሻንሲ ቁጥር |
የስሪት ቁጥር |
||||||
|
1 |
ዲ.ኤ.ቲ አስመጪና ላኪ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር
|
ዲ.ኤ.ቲ አስመጪና ላኪ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር
|
ሻላ
|
03-B71237 አአ
|
አውቶሞቢል
|
K12MP-4278995
|
MBHCZF6 3S00165185
|
2021
|
2,400,000.00
|
ጨረታው የሚከናወነው በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሰኔ 04 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00-10፡00 ድረስ ይሆናል: |
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (CPO) ብቻ በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ/ማ ስም በማሰራትና ለጨረታ ማስከበሪያነት በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
- የተጫራቾች ምዝገባ የሚከናወነው ጠዋት ለሚካሄደው ጨረታ ከስዓት 8፡00-9፡30 ድረስ ይሆናል:: ምዝገባ ከተጠናቀቀ በኋላ ለንብረቱ የሚመደበው የጥሪ ስዓት 30 ደቂቃ ብቻ ሲሆን የጨረታው ማጠናቀቅያ ስዓት ድረስ ኣሸናፊው ካልተለየ ኣሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል።
- በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ከሚያካሂደው የባንኩ የህግ አገልግሎት መምሪያ ሕግ ኣገልግሎት ዋና ክፍል ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል።
- የጨረታው አሸናፊ ቀሪውን ገንዘብ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ካሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ ይከፍላል።
- ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት አስቀድሞ ጨረታው በሚካሄድበት ቦታ ከሚገኘው የባንኩ ቅርንጫፍ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል።
- በሐራጅ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዥ ወይም የነዚህ ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው:: ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዦች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታዉን ሂደት ለመከታተል በተጠቀሰዉ ቦታ እና ሰዓት እንድትገኙ እያሳሰብን ካልተገኛችሁ በሌላችሁበት ጨረታው የሚከናወን መሆኑን እንገልፃለን።
- ባንካችን ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል።
- ከሚሸጠው ንብረት ጋር የተያያዙ ከጨረታው በፊትም ሆነ በኋላ ማንኛውም ለመንግስት ሊከፈሉ የሚገባቸው ተ.እ.ታን ጨምሮ ማንኛውም አይነት ክፍያዎች፣ ወጪዎች ወይም የግብር ክፍያዎች እንዲሁም በንብረት ማስተላለፍ ሂደት የሚመጡ የአሹራ፣ የእግድ ማንሻ፣ የቦሎ፣ የስም ማዘዋወሪያ ክፍያዎችን ጨምሮ ማንኛውም አይነት ክፍያዎች ወይም ግብር ሙሉ በሙሉ የጨረታ አሸናፊው/ገዥው/ የሚሸፍን ይሆናል።
- ባንኩ ከጨረታ በፊት ሆነም በኋላ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ ማብራርያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት ጨረታው በዋና መስሪያ ቤት በኩል ለሚካሄደው ንብረት በዋና መስሪያ ቤት -ሕግ መምሪያ በኩል ወይም በስልክ ቁጥር +251116627120 መረጃ መጠየቅ ይቻላሉ::
አንበሳ ባንክ አ.ማ.
Tender details
- Deadline: 2026-06-11
- Bid closing time: 16:00
- Bid opening: 2026-06-11 16:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Anbesa Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published: May 24, 2026
- Posted at: 2026-05-25T12:52:09.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.