ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ለዋና መ/ቤት ህንፃ ግንባታ ሲጠቀምበት የነበረውን ቁርጥራጭ እንጨቶች እና ፕላይዉድ (ሳፋሪያን) ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

(Ref No. TISC/ HRPA/017/2026)

ኩባንያችን ለዋና መ/ቤት ህንፃ ግንባታ ሲጠቀምበት የነበረውን ቁርጥራጭ እንጨቶች እና ፕላይዉድ (ሳፋሪያን) ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

  • ለመሸጥ የተዘጋጁትን ቁርጥራጭ እንጨቶች እና ፕላይዉድ (ሳፋሪያን) ፒያሳ አዲስ አበባ ሬስቶራንት ፊት ለፊት በሚገኘው የኩባንያው ህንፃ ከግንቦት 17/2018 ዓ.ም ጀምሮ በአካል በመገኘት እና በማየት የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 25/09/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የቀድሞው ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ዋና መ/ቤት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ በማድረግ መጫረት ይችላሉ።
  • ጨረታው ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8:30 ተጫራቾች በተገኙበት የሚከፈትይሆናል።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ቦሌ ከሚገኘው የኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 106 በአካል በመገኘት መውሰድ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  • በሌሎች ተጫራቾች በተሰጠ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ወይም ተመስርቶ ዋጋ ማቅረብ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
  • የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% በተጨማሪነት ይከፍላሉ።
  • የጨረታው አሸናፊዎች ውጤት ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያውን በመፈፀም ንብረቱን ከቦታው ሙሉ በሙሉ ማንሳት ይኖርባቸዋል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክፍያ የማይፈጽሙ አሸናፊዎች ያስያዙት CPO ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 111 9771/70/ 09 68 58 00 08 በመደወል ወይም ከላይ በተጠቀሰው ዋና መ/ቤት በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል።
  • ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ.


Tender details

  • Deadline: 2026-06-02
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-06-02 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Tsehay Insurance S.C.
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
  • Published: May 24, 2026
  • Posted at: 2026-05-25T12:54:43.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders