ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ. የካሳ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን ከባድና ቀላል የተጎዱ ተሽከርካሪዎች ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ውጫዊና ውስጣዊ አካላት ቅሪቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ

Abay Insurance S.C

1. ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ የካሳ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን ከባድና ቀላል የተጎዱ ተሽከርካሪዎች ልዩ ልዩ የተሸከርካሪ ውጫዊና ውስጣዊ አካላት ቅሪቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

2. ተሸከርካሪዎቹን ፤ ውጫዊና ውስጣዊ አካላት ቅሪቶችን ለመግዛት በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ሁሉ ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በቅድሚያ ከፍሎ ከዋናው መ/ቤት በመግዛት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ከሃናማርያም አደባባይ ወደ ቃሊቲ በሚወስደው ቀለበት መንገድ 800 ሜትር ወረድ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው ሪከቨሪ በመቅረብ ከግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በስራ ሰዓት ብቻ በመምጣት ማየት ይቻላል

3. ተጫራቾች ተሽከርካሪውን ወይም እቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ከግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 3.00 ሰዓት ድረስ አትላስ አካባቢ በሚገኘው የአባይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የሚጫረቱበትን ዕቃ ኮድ በጨረታው ፖስታ ላይ በመጻፍ የሚወዳደሩበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች ዝቅተኛ ማስያዣ ብር 1,000.00 ሆኖ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 15% በ CPO የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። በጨረታው ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ሶስት የስራ ቀናት በኃላ ተመላሽ የሚደረግ ይሆናል።

5. የጨረታው አሸናፊዎች የተሸከርካሪዎችንም ሆነ የዕቃዎችን ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በመክፈል ተሸከርካሪዎችንና እቃዎችን በ10 ቀናት ውስጥ ባይረከቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።

6. ተሽከርካሪዎች በጨረታ እስከተሸጡበት ጊዜ ድረስ የሚፈለግ ግብርና ታክስ ቢኖር የሻጭ ኃላፊነት ይሆናል። ተሸከርካሪዎቹ ከተሸጡ በኋላ የሚፈለግ ግብርና ታክስ፣ ስም ማዛወርያ እንዲሁም ሌላ ክፍያ ቢኖር የገዢው ኃላፊነት ይሆናል።

7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለዚሁ በተዘጋጀ ቅፅ መሰረት የሚገዙትን ዕቃ ዋጋና 15% የተጨማሪ እሴት ታክስን በግልጽሁኔታ በተናጥል ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. ከቀረጥ ነፃ ተሸከርካሪዎችን ኩባንያው ለገዢዎች የሚያስረክበው ገዢዎች በቅድሚያ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሚወስነውን ቀረጥና ታክስ ክፍያ ከፍለው ተገቢውን ማስረጃ ሲያቀርቡ ብቻ ይሆናል።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹንም ሆነ ሌሎች ዕቃዎችን ከሪከቨሪ በራሳቸው ወጪ ሳይነጣጥሉ በጠቅላላ በአንድ ጊዜማንሳት ይኖርባቸዋል።

10. ጨረታው ቅዳሜ ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ይከፈታል። ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ 011 515 4507፣ 011 551 0817 ፣ 011 553 5300 ፣ 0913 57 01 55 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

 


Tender details

  • Deadline: 2026-06-06
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid opening: 2026-06-06 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Abay Insurance S.C.
  • Bid bond: ዝቅተኛ ማስያዣ ብር 1,000.00 ሆኖ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 15% በ CPO የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published: May 24, 2026
  • Posted at: 2026-05-25T12:57:19.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders