በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የኖራ ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የኖራ ግዥ ጨረታ  ማስታወቂያ 177/18

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ለግብርና ግብዓት ገጠ/ፋ/ዘርፍ የኖራ ግዥ በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተዘረዘረው መሰረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ተ/ቁ

የዕቃው አይነት

መለኪያ

ብዛት

የጨረታ  ማስከበሪያ

የሚታሸግበት ሰዓት

ሰነዱ የሚገኝበት ቦታ

1

ኖራ ከነትራንስፖርቱ እና ጫኝ እና አውራጅን ጨምሮ

በኩ/ል

 

15,400

200,000

 

በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል

ደ/ኢ/ግ/ቢሮ ዲላ መምህራን ኮሌጅ ግቢ

በንግድ ስራ ዘርፉ የታደሰ ፍቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና የቫት መዝጋቢነት ማስረጃዎች ያላቸውና የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል።
  • በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ-ፒ-ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያሲያዙበትን ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች በቢሮ የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው ተከታታይ እስከ 16ኛ ቀን 11፡30 ድረስ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በዲላ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ መምህራን ኮሌጅ ግቢ ከሚገኘው የግብርና ቢሮ ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ በመሙላት ይህ የጨረታ የቴክኒካልና ፋይናሻል የማጫረቻ ሰነዶች በአንድነት ፖስታ በማዘጋጀት በ 16ኛው ቀን 4፡ዐዐ ሰዓት በቢሮ ግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል። እንዲሁም የጨረታው ሳጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች (ተወካዮቻቸው) በተገኙበት በቢሮው የግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ይከፈታል።
  • ከ200,000 ሺ ብር በላይ ለሆነ ግዥዎች ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
  • ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ ካሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20% ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
  • የጨረታው ሳጥን መክፈቻ በ16ኛው ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣይ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
  • ሁለት ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ዋጋቸው እኩል በሚሆንበት ወቅት በእጣ የሚለይ ይሆናል።
  • ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ 046-131 0134 ይጠቀሙ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-08
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-08 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: South Ethiopia Region Agriculture Bureau
  • Bid bond: 200,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: May 24, 2026
  • Posted at: 2026-05-25T13:59:42.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders