የተፈጥሮ ፈሳሽ ማዳበሪያ ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ማ በተለያዩ ክልሎች ድርጅቱ ያወጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ጠንካራና ለአርሶ አደሩ የሚታመኑ አከፋፋዮችን አወዳድሮ ውክልና መስጠት ይፈልጋል
Description
የተፈጥሮ ፈሳሽ ማዳበሪያ ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ማ
Organic Liquid Fertilizer Producing PLC
ቁጥር: OLF/GM/122304/2018
ማስታወቂያ
ድርጅታችን ኢኮ ግሪን-ኦርጋኒክ ሊውኪድ ፈርቲላይዘር ፕሮዲውሲንግ ፒ.ኤል.ሲ ብቸኛ የፈጠራ ባለቤት እና ፈሳሽ ማዳበሪያን በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በማምረት ለባለፉት አስራ አምስት አመታት በላይ በሀገራችን አርሶ አደሮች ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው ሲሆን፣ ከምርቱ ከፍተኛ ፍላጎት በመነሳት በተለያዩ ክልሎች ድርጅቱ ያወጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ጠንካራና ለአርሶ አደሩ የሚታመኑ አከፋፋዮችን አወዳድሮ ውክልና መስጠት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች ወኪል መሆንና ምርታችንን ማከፋፈል የምትችሉ መሆኑን በታላቅ ደስታ እናበስራለን።
- በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፣ እንዲሁም በዘርፉ የወጣውን የንግድ መስፈርት ሙሉ በሙሉ የምታሟሉ፣
- ምርቱን በማሰራጨት ሂደት በአካባቢው ጠንካራ የገበያ ትስስርና ተቀባይነት ያለው፣
- ታማኝ ጠንካራና ከትርፋማነት ባለፈ አርሶ አደሩን ለማገዝ አቋምና ህልም ያለው፣
- በረጅም ጊዜ የንግድ አጋርነት የሚያምን፣ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ዝግጁ የሆነ፣
የሽያጭ ወኪሉ የሚፈለግባቸው ቦታዎች፡- በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች ሲሆን ወኪሉ በመረጠው ክልል/ከተማ ላይ ማመልከት ይችላል።
አመልካቾች ከላይ የተገለጹትን ዝርዝር መስፈርቶች የምታሟሉ ከሆነ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት አስር የስራ ቀናት ቦሌ ሚሊኒም አዳራሽ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው ቢሮዋችን በአካል በመቅረብ በተዘጋጀውን የውል ፎርም ሞልታችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።
‹‹ ኢኮ ግሪን ለዘላቂ የግብርና ልማት ! >>
ድርጅቱ!
Tender details
- Deadline: 2026-06-13
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት አስር የስራ ቀናት
- Bid opening: 2026-06-13 17:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የተፈጥሮ ፈሳሽ ማዳበሪያ ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ማ
- Buyer address: 22 አደባባይ፣ናዝሬት ህንጻ 4ኛ ፎቅ
- Published: Jun 03, 2026
- Posted at: 2026-06-03T11:16:25.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.