ዳንኤል ተስፋይ አስመጪ በተለያየ ግዜ ከዉጭ ሀገር ያስመጣቸዉ እና በተለያየ ምክንያት ያልተሸጡ የሞባይል ከቨር (Mobile Cover) እቃዎች በጨረታ አወዳደወሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:-DTI/001/2018

ድርጅታችን ዳንኤል ተስፋይ አስመጪ በተለያየ ግዜ ከዉጭ ሀገር ያስመጣቸዉ እና በተለያየ ምክንያት ያልተሸጡ የሞባይል ከቨር ( Mobile Cover ) እቃዎች በጨረታ አወዳደወሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በዘርፉ ላይ የተሰማራቹ በጨረታዉ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ የማይመለስ ብር 300.00 ( ሶስት መቶ ብር ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን መግዛት የምትችሉ ሲሆን ተጫራቾች ሟሟላት የሚገባቸዉ።

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉ እና ኮፒዉን ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እና የስራ መለያ ቁጥር ቲን ቁጥር እና ኮፒዉን ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጫራች ድርጅቶች የጨረታ ማስከበርያ የተጫረተበትን ከጠቅላላ ዋጋ 5% በ CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በ ዳንኤል ተስፋይ በሚል ስም በማሠራት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ማንኛዉም ተጫራች ሌላዉ ተጫራች ባቀረበዉ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
  5. ከጨረታዉ መክፈቻ ቀንና ሰአት ካለፈ ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የጨረታ ሰነዱን ቃሊቲ ማሰልጠኛ ዴልታ ኮምፕሌክስ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 213-A ላይ ከሚገኘው ከሰኞ እስከ አርብ በሥራ ሰአት መግዛት ይችላሉ። ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛዉ ቀን እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊልም መሰረዝ ይችላል፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911058910/0911222033 መጠየቅ ይችላሉ።

ዳንኤል ተስፋይ አስመጪ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-08
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛዉ ቀን እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት
  • Bid opening: 2026-06-08 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛዉ ቀን እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ዳንኤል ተስፋይ አስመጪ
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: May 24, 2026
  • Posted at: 2026-05-25T14:11:04.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders