የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በሚገኘው የአሶሳ ቅ/ጽ/ቤት ካምፓስ አካባቢ ባለዉ ቅጥር ግቢ እና መጋዘን የሚገኙትን የተለያዩ፤ ያገለገሉ እና አዲስ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- አሶሳ/ስተአ/002/2018

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በሚገኘው የአሶሳ ቅ/ጽ/ቤት ካምፓስ አካባቢ ባለዉ ቅጥር ግቢ እና መጋዘን የሚገኙትን የተለያዩ ፤ያገለገሉ እና አዲስ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ በድጋሚ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች

  1. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የአሶሳ ቅ/ጽ/ቤት በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መ/ቤት ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁጥር 7 በመገኘት እና ክፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ከግንቦት 18/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 28/ 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።
  2. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት/Refugees and Returnees Service /በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ የባንክ ዋስትና / Bank Gurantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራጭ ከግንቦት 18/2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 28/2018 ዓ/ም ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት አሶሳ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት ይችላል። ቅዳሜ እና እሁድ የመስሪያ ቤቱ ስራ ቀናት አይደሉም።
  4. ጨረታው አሶሳ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ግንቦት 28 ከቀኑ 7፡30 ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
  5. የጨረታ አሸናፊ ተጫራቶች ለጨረታው ያሰያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያሰያዙት የጨረታ ዋስትና በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  6. ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው፡፡
  7. በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ለሽያጭ በተዘጋጀው ጨረታ ሰንድ ላይ በተራ ቁጥር 94 የተጠቀሰው ኮንቴይነር ከአሶሳ ከተማ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ሽርቆሌ ስደተኞች ማእከል ወይም ኩቡሪ ሃምሳ ይገኛል።
  10. ለሽያጭ በተዘጋጀው ጨረታ ሰንድ ላይ በተራ ቁጥር 149 የሚገኙት 2 ባለ 50000 ሊትር የነዳጅ ታንከር ከአሶሳ ከተማ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ሽርቆሌ ስደተኞች ማእከል እና በባምባሲ ስደተኞች ማእከል ወምባ ቀበሌ ይገኛሉ።
  11. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251952823095 ወይም 0577752465 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።

አድራሻ፡- ከልል ፖሊስ ኮሚሽን አካባቢ ዉሃና ፍሳሽ ጎን

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት

አሶሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-05
  • Bid closing time: 13:30
  • Bid opening: 2026-06-05 14:00
  • Region: Beneshangul Gumuz
  • Publishing entity: Refugee and Returnee Service
  • Buyer address: ከዋሽንግተን የህክምና ማዕከል 500 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ላይ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 24, 2026
  • Posted at: 2026-05-25T14:19:17.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders