የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የጋምቤላ ቅ/ጽ/ቤት ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ዕቃዎችን ለመሸጥ በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በጋምቤላ ከተማ በሚገኘው የጋምቤላ ቅ/ጽ/ቤት እና የስደተኛ ማዕከል ቅጥር ግቢ እና መጋዝን የሚገኙትን ከዚህ በታች በተጠቀሱት ሎቶች መሰረት ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

.

የሎት(Lot) ቁጥር

የእቃዎቹ ዓይነት

የጨረታ መለያ ቁጥር

1

ሎት አንድ

 

ፌሮ ብረቶች፣ ሴራሚኮች፣ ጎማዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የውሃ ዕቃዎች የሻወርና የመፀዳጃ ቤት ዕቃዎች እና ሌሎችም ተዛማጅ ዕቃዎች

ጋምቤላ ስተአ/001/2/18

 

2

ሎት ሁለት

 

ላፕቶፕ፣ ዴስክቶፐ፣ ፕሪንተር፣ እስካነር፣ ቴሌቪዥን፣ ፍሪጅ፣ ሞንታርቦ፣ ኤሲ፣ ሚስማሮች፣ ብረቶች እና ሌሎችም ተዛማጅ ዕቃዎች

ጋምቤላ/ስተአ/002/2/18

 

 

ሎት ሦስት

 

የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እና የህንፃ መሳሪያ ዕቃዎች (ላፕቶፕ፣ ዴስክቶፕ፣ ፕሪንተር፣ እስካነር፣ ቴሌቪዥን፣ ፍሪጅ፣ ሞንታርቦ፣ ኤሲ፣ ሚስማሮች፣ ብረቶች፣ ኮንቴነር እና ሌሎችም

ጋምቤላ/ስተአ/003/2/18

 

በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ በድጋሚ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-

1) ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጋምቤላ ቅ/ጽ/ቤት በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መ/ቤት ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁጥር 7 በመገኘት እና ክፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ከግንቦት 18/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 28/ 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።

2) በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት/ Refugees and Returnees Service /በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ የባንክ ዋስትና /Bank Gurantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3) ማንኛውም ተጫራች ከግንቦት 18/ 2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 28/2018 ዓ/ም ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ጋምቤላ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅ/ፅ/ቤት ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት ይችላል። ቅዳሜ እና እሁድ የመስሪያ ቤቱ ስራ ቀናት አይደሉም።

4) ጨረታው ጋምቤላ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅ/ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ግንቦት 28 ከቀኑ 7፡30 ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።

5) የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያሰያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያሰያዙት የጨረታ ዋሰትና በ3 ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

6) ተጨራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው።

7) በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጨራች ለጨረታው ማስከበርያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8) አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9) ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 91 127 8481 ወይም +251 91 046 4495 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-05
  • Bid closing time: 13:30
  • Bid opening: 2026-06-05 14:00
  • Region: Gambela
  • Publishing entity: Refugee and Returnee Service
  • Buyer address: ከዋሽንግተን የህክምና ማዕከል 500 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ላይ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: May 25, 2026
  • Posted at: 2026-05-26T06:49:58.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders