የጉራጌ ሕዝብ ራስ አገዝ ልማት ድርጅት (ጉሕራልድ) በወልቂጤ ከተማ ግቢ ውስጥ የሚገኙ ያገለገሉ ላንድሮቨሮች፣ የመለዋወጫ ዕቃዎችን፣ Old Model Desktop Computers፣ ሞተር ሳይክሎች እና በኪሎ ግራም የሚመዘኑ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጉራጌ ሕዝብ ራስ አገዝ ልማት ድርጅት (ጉሕራልድ) በወልቂጤ ከተማ ግቢ ውስጥ የሚገኙ ያገለገሉ ላንድሮቨሮች፣ የመለዋወጫ ዕቃዎችን፤ Old Model Desktop Computers፣ ሞተር ሳይክሎች እና በኪሎ ግራም የሚመዘኑ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል። 

በመሆኑም ጨረታውን መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ሁሉ፡-

1. ዘወትር በሥራ ቀናት ከግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በግቢው ውስጥ መመልከት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ወልቂጤ ከሚገኘው ቅ/ጽ/ቤትና አዲስ አበባ ከሚገኘው ዋና መ/ቤት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ።

3. በጨረታ ለመወዳደር ያቀረቡትን የመነሻ ዋጋ የጠቅላላ ዋጋውን 10 (አሥር በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ገቢ ያደርጋሉ። በጨረታው ላሸነፉ ከግዥ ዋጋው ተቀናሽ ተደርጎ በታሳቢነት ይያዝላቸዋል።

4. በጨረታው ለተሸነፉ ከውድድር ውጤት በኋላ ሲፒኦው ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

5. የጨረታው ሳጥን ሰኔ 02 ቀን 2018 ዓ.ም ሰኞ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ በድርጅቱ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ግንቦት 02 ቀን 2018 ዓ.ም በጊዜያዊ ጨረታ ኮሚቴ ይከፈታል።

6. አሸናፊዎች በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ከፍያ አጠናቀው ንብረቱን ባይረከቡ ለጨረታ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።

7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ለአሸፊዎች በውስጥ ማስታወቂያ ይገለጻል።

ማንኛውም ተጫራች ማብራሪያ ከፈለገ በሚከተሉት አድራሻዎች መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ፡

1. የጉራጌ ሕዝብ ራስ አገዝ ልማት ድርጅት አዲስ አበባ፤ አትክልት ተራ በስልክ ቁጥር 09 11 73 50 22 ወይም 09 11 22 00 44
2. ወልቂጤ ቅ/ጽ/ቤት ወይም በስልክ ቁጥር 09 13 87 29 46 ወይም 09 14 34 14 06

የጉራጌ ሕዝብ ራስ-ገዝ ልማት ድርጅት(ጉሕራልድ)


Tender details

  • Deadline: 2026-06-09
  • Publishing entity: የጉራጌ ሕዝብ ራስ-አገዝ ልማት ድርጅት  (ጉሕራልድ)
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published: May 25, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders