የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሽከርካሪ ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

በአፈ/ከሣሽ አቶ ታከለ ቅጣው እና በአፈ /ተከሣሽ የሰ/ሸዋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት መካከል ስለአለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ መካከል ስለአለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የአፈጻጸም ተከሣሽ ንብረት የሆነው የሰሌዳ ቁጥሩ አማ-04-07364 ፒክአፕ ተሽከርካሪ ሞዴል H2J79L-JTMRS፣ የሞተር ቁጥሩ 1HZ-0982217 የሻንሲ ቁጥር JTERB71J80B28499 ለህዝብና ለጭነት(ለድርብ ተግባር) አገልግሎት የሚውል የመጫን አቅሙ 7 ኩንታል ወይም 4 ሰው የሚጭን አቅም ያለው እና አመታዊ የምርመራ ቁጥሩ 22/01/2018 ዓ.ም የሆነ ተሽከርካሪ መኪና በጨረታ መነሻ ዋጋ 3,226,150 /ሶስት ሚሊየን ሁለት መቶ ሃያ ስድስት ሺህ አንድ መቶ ሃምሣ ብር/ በሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል።

በመሆኑም፡-

1. ተጫራቾች ከጫራታው በፊት የግምቱን 1/4ኛውን በሲፒኦ ለሀራጅ ባዩ የማስያዝ ግዴታ አለባቸው።

2. ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

3. ንብረቱን ለመሸጥ ምክንያት የሆነው ለፍርድ ማስፈፀሚያ ነው።

4. ገዥው በጨረታ ለገዛው ንብረት ዋጋውን ሣይከፍል የቀረ እንደሆነ ወይም በህግ በተወሰነው በዚሁ የሽያጭ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው መሠረት ዋጋውን ያላስቀመጠ እንደሆነ ሽያጩ ይሠረዛል በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/429/2/ መሠረት ለሃራጅ ማስታወቂያው የተደረገውን ወጪ እንዲከፍል ይገደዳል።

5. የሐራጅ ማስታወቂያውን ለማቋረጥ የሚቻልበት የተሻለ መንገድ ካለ የጨረታ ማስታወቂያው በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ ይችላል።

ደ/ብርሃን

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-26
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-06-26 12:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: ANRS North Shewa Zone High Court
  • Bid bond: 25%
  • Published: May 25, 2026
  • Posted at: 2026-05-26T07:25:38.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders