አማራ ፓይፕ ፋብሪካ የግል ኩባንያ በበጀት ዓመቱ የERP Software የተገበረ ሲሆን የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ እንቅስቃሴውን በIFRS መሠረት በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው የሂሳብ ምርመራ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማስመርመር ይፈልጋል

Description

የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር-APF/22/2018/Local

አማራ ፓይፕ ፋብሪካ የግል ኩባንያ በበጀት ዓመቱ የERP Software የተገበረ ሲሆን የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ እንቅስቃሴውን በIFRS መሠረት በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው የሂሳብ ምርመራ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማስመርመር ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች -

1. ለ2018 በጀት ዓመት በሙያው የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የተሰጠ የታደሰ የኦዲት ሙያ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት እና VAT ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከፋብሪካው የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

3. ተወዳዳሪ ድርጅቶች የተወዳደሩበትን የአገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ VATን ጨምሮ 2% ባህርዳር ከተማ ውስጥ ባለ የባንኩ ቅርንጫፍ በኩል ማረጋገጫ የተሰጠበት የጨረታ ማስከበሪያ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Irrevocable & unconditional Bank Guarantee) በፋብሪካው ስም “Amhara Pipe factory Plc" በማሰራት ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራቾች የሕጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ኮፒ እና ሌሎች የቴክኒክ መወዳደሪያ ሠነዶችን በአንድ ላይ (Technical Bid Offer) በማለት ለብቻው ከዋጋ ማቅረቢያው (Financial Bid Offer) በመለየት በፖስታ በማሸግ (ዋና ወይም ቅጂ ብሎ በጽሑፍ በመለየት) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. እንዲሁም ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን (Financial Bid Offer) እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን ለብቻው ከላይ በተ.ቁ.4.1 ላይ ከተገለፁት ከቴክኒክ መስፈርት በመለየት በፖስታ በማሸግ (ዋና ወይም ቅጂ ብሎ በጽሑፍ በመለየት) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ15ኛው ቀን ቢሮ ቁጥር 206 ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 የቴክኒክ የመጫረቻ ሠነድ ብቻ ይከፈታል።

7. 15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የሕዝብ በዓል ቀን ከሆነ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይሆናል።

8. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ፋብሪካው ድረስ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 09-35-98-37-29 / 09-18-70-18-26 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግ/ ኩባንያ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-09
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-09 14:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara Pipe Factory PLC
  • Buyer TIN: 0006196550
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: May 25, 2026
  • Posted at: 2026-05-26T07:30:54.000Z
  • Buyer website: https://amharapipe.et/

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders