የአዲስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሚ ኩራ ምድብ ችሎት ቶዮታ ኮሮላ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው መስፈርት
የፍ/ባለመብት ፋንታነሽ ገብሩ የፍ/ባለእዳ ወ/ሮ ትዕግስት አበበ መካከል ስላለው የፍ/አፈፃፀም ጉዳይ በፍርድ ባለዕዳ ተመዝግበው የሚገኘው ቶዮታ ኮሮላ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
- በጨረታ የሚሸጠው መኪና ቶዮታ ኮሮላ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-A27859 አ.አ፤ የሻንሲ ቁጥር NZE120-3050002 ፤ የሞተር ቁጥር 2NZ-3128727:
- የተመረተበት ሀገር ጃፓን
- ተሽከርካሪ የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 658,275.84 (ስድስት መቶ ሃምሳ ስምንት ሺህ ሁለት መቶ ሰባት አምስት ብር ከሰማኒያ አራት ሳንቲም)።
- በጨረታ መግዛት የሚፈልግ ሰው በሙሉ የጨረታ ሰነድ ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር ከፍሎ መግዛት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ለጨረታው የጨረታ ማስከበሪያ 50,000(ሃምሳ ሺህ) ብር በሞዴል 85 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት ሂሳብ ቁጥር ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ገንዘቡ ጨረታውን ላሸነፈው ከመኪናው ግዥ ሂሳብ ላይ የሚካተትለት ወይም የሚመለስለት ሲሆን ጨረታውን ላላሸነፉ ከጨረታው በኃላ ወዲያው ተመላሽ የሚደረግላቸው ይሆናል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አንድ ወር ግዜ የሚቆይ ይሆናል።
- መኪናውን በጨረታ መግዛት የሚፈልግ አካል የጨረታ ሰነድ ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት የጨረታ ሰነድ በ500 ብር ከገዛ በኃላ እንደገና በአደስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት ሂሳብ ቁጥር ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ 50,000(ሃምሳ ሺህ) ብር በሞደል 85 በማስገባት የሚወዳደርበትን የመኪናው ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ አሽጎ ለሰሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርበታል።
- የጨረታው ሰነድ የጨረታ ኮሚቴ እና ተጫራቾች ባሉበት የሚከፈት ይሆናል። ይህም በውስጥ ማስታወቂያ ከአዲስ ዘመን የጋዜጣ ማስታወቂያ በኃላ የሚነገር ይሆናል።
- የመኪናውን ይዞታ እና ሞዴል ለማወቅ የፈለገ አካል መኪናው ተይዞ ባለበት በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ማየት ይችላል።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 251-11 650 6205 ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ይደውሉ።
የአዲስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሚ ኩራ ምድብ ችሎት
Tender details
- Deadline: 2026-06-26
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አንድ ወር ግዜ የሚቆይ ይሆናል
- Bid opening: 2026-06-26 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City first instance court lemi kura Court
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: May 25, 2026
- Posted at: 2026-05-26T08:16:18.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.