በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮንክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅና በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ
ተሽከርካሪዎችንና ሰዩ ስቦ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 54/2018
በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፤ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ እንዲሁም ንብረቶችን
- የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣
- ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣
- የኤሌክትሮንክስ ዕቃዎችን፣
- የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣
- የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፤
- የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና
- ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅና በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ከዚህ በታች በቅጹ ከተጠቀው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከአርብ ግንቦት 21/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን።
በመሆኑም
1. በተሸከርካሪ ግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል።
2. በዕቃ ግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሲሆን ለሐራጅ ጨረታ ደግሞ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል።
3. በጨረታው ላይ የተሽከርካሪ ወይም የዕቃው አስመጪጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም።
4. ተጫራቾች የተሽከርካሪውንና የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከአርብ ግንቦት 21/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
5. በዕቃና ተሽከርካሪ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ወይም ተሸከርካሪዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንከ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. የዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለዕቃዎች ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተ.ቁ 5 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት። ነገር ግን በዕቃ ሐራጅ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጹ የተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) መጠን የሚወሰን መሆኑን እንገልጻለን።
7. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው ዓይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት |
የዕቃ ሐራጅ |
እስከ 25/09/2018 |
26/09/2018 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል። |
|
የዕቃ ግልፅ |
እስከ 25/09/2018 |
26/09/2018 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል። |
||
|
የተሽከርካሪ ግልጽ |
እስከ 26/09/2018 |
27/09/2018 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል። |
8. የጨረታው መከፈቻ ቦታ፡-ኢአ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
9. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
10. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሳት ይኖርባቸዋል።
11. ከላይ በተ/ቁ 10 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረከበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
12. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩከ ፡- 011-470-8503
አድራሻ፡ ሳሪስ አቦ ቤ/ከ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መገንጠያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ
በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-03
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-06-04 10:00
- Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa Kality Customs Branch Office
- Buyer address: ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: May 25, 2026
- Posted at: 2026-05-26T08:23:41.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.