የቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የደንብ ልብስ ስፌት የእጅ ዋጋ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰፋት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2018 ለሥራ የሚገለገልበትን :-
Lot.1. የደንብ ልብስ ስፌት የእጅ ዋጋ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰፋት ይፈልጋል።
የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
1. ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (VAT) ያላቸው።
3. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አከላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስራ አምስት /15/ተከታታይ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል በመ/ቤቱ ቀርቦ መግዛት ይችላሉ።
5. ለጨረታው ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት የዕቃ ዋጋ ብር 1% በተረጋገጠ ባንክ (cpo) በድርጅቱ ስም አሰርቶ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል።
6. የደንብ ልብሱ ስፌት የሚሰፋው በድርጅቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ነው።
7. ለስራ የሚያገለግሎትን እቃዎች በራሱ ወጪ ድርጅቱ ቅጥር ጊቢ ማምጣት ይኖርበታል።
8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የእቃውን ስፔስፊኬሽን ከድርጅቱ በቀረበው መሠረት በግልፅ በመፀፍና ዕቃው ላይም በግልፅ መታየት ይኖርባቸዋል።
9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።
10. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት 15%(Vat )ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን አሟልተው በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ቀርቦ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ በ15ኛ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
11. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ተከታታይ ቀናት ጠብቆ በ15ኛ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በዛው ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። በእለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
12. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
13. ድርጅቱ ከሰጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ ማስተካከያ ማድረግ እናመሰረዝ(Materia Devation) አይቻልም ተጫራቾች በድርጅቱ በዋጋ ማቅረቢያ የድርጅቱ ኦርጅናል ማህተም የቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎትድርጅት የሚል ማህተም ባረፈበት ላይ ቢቻ የዕቃ ዋጋዎችን ሞልቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ከድርጅቱ ዋጋ ማቅረቢያ ውጪ የሚመጡ ሰነዶች ዋጋ የላቸውም።
14. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
15. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ድርጅታችን ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክተር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011- 437-1683 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
የቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃ
እና ፍሳሽ አገልግሎትድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-06-09
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-09 14:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛ ቀን 8፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: ቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልገሎት ድርጅት
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: May 26, 2026
- Posted at: 2026-05-26T08:37:43.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.