የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ስር በተለያዩ ቦታዎች ተከማችተው የሚገኙ ተቀቅለው ያገለገሉ የእንጨት ምሶሶዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ሰሜ/አ/አ/ሪ/ግ/ጨ/010/2018

የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ስር በተለያዩ ቦታዎች ተከማችተው የሚገኙ ተቀቅለው ያገለገሉ የእንጨት ምሶሶዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

.

የእቃው ዓይነት

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ

1

ተቀቅለው ያገለገሉ የእንጨት ምሶሶዎችን

ግንቦት 26 ቀን 2018 . 800 ሰዓት

ግንቦት 26 ቀን 2018 . 830 ሰዓት

 

ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር)

ማሳሰቢያ፡- የእንጨት ምሶሶዎችን በተመለከተ ፈፅሞ ለማገዶነት (ለምግብ ማብሰያነት) እና ለኤሌክትሪከ መሰመር ዝርጋታ የማያገለግሉ ሲሆን ለመግዛት  የሚቀርቡ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ግዥውን ፈፅመው ከወሰዱ በኃላ በሰው፣ በእንሰሳት እና በተፈጥሮ (አካባቢ) ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ በኃላፊነት መልሰው በሥራ ላይ የሚያውሉ መሆንና በዚሁ አግባብም እንደሚጠቀሙ በደብዳቤ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።

1. ማንኛውም የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የትኛውም አካል እና ማንኛውም የንግድ ፍቃድ የሌለው ግለሰብ የጨረታ ሰነድ ገዝቶ የጨረታ ዋስትና በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000149984384 (EEUN/A/A/R CUCON FOR ELCON) በሚለው ገቢ በማድረግ እና የከፈሉበትን የባንክ ስሊፕ ይዞ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።

3. አድራሻ፡- ፒያሳ አቡነጴጥሮስ ፊት ለፊት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር-210 በሚገኘው ሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ግዥ እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ፣

4. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በተገለፀው መሠረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ሰሜ/አ/አ/ሪ/ግ/ጨ/010/2018 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ስዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፣

6. ጨረታው ከላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣

7. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 84 82 00 07 መደወል ይችላሉ።

8. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-03
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-06-03 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Electric Utility
  • Bid bond: 25,000.00 ብር
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published: May 26, 2026
  • Posted at: 2026-05-26T08:40:00.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders