የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ስር ያሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን የጥገና አገልግሎት በቅርበት ለመስጠት የጋራዥ ግልጽ ጨረታ አውጥቷል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ስር ያሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን የጥገና አገልግሎት በቅርበት ለመስጠት የጋራዥ ግልጽ ጨረታ አውጥቷል።
ስለሆነም በዘርፉ ልምድ ያላቸው እና ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች በሚከተሉት መስፈርቶች መሰረት እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።
1. የጨረታው አይነት
የተለያዩ የተሽከርካሪዎች ጥገና ፡
- ቪ-8፣ ላንድ ክሩዘር ፣ ሀርድ ቶፕ፣ ኮብራ ስቴሽን ዋገን፣ ፕራዶ፣ኒሳን አልሜራ፣ሂኖ የጭነት መኪና ሃይ ሩፍ ሚኒ ባስ፣ ሚስቲ ቡሽ ፣ማህንድራ፣ ቢሾፍቱ እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች
2. የተጫራቾቾ መስፈርት፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው
- የTIN ቁጥር እና የVAT ተመዝጋቢ የሆነ
- ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የጥገና ፈቃድ ሰርተፊኬት ያለው
- በተሽከርካሪ ጥገና ስራ በቂ ልምድ ያለው
- የስራ ማስረጃ እና የቀድሞ ደንበኞች ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
3, የጨረታ ሰነድ መግዣ፡-
የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት አምስት መቶ ብር በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መግዛት ይቻላል።
4. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ፡-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአንድ በማሸግ ዘወትር በስራ ሰአት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን፤ ለጨረታው ማስከበሪያ አንድ መቶ ሺህ ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
5. የጨረታ መክፈቻ፡-
ጨረታው ከቀኑ ስድስት ሰአት ታሽጎ በዛው እለት ከቀኑ ስምንት ሰአት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በአል፣ ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በስምንት ሰአት ይከፈታል።
6. ማሳሰቢያ
- ድርጅቱ የተሻለ ጥቅም ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
- የጨረታ ሰነዶች ዘግይተው ከቀረቡ ተቀባይነት አይኖራቸውም።
አድራሻ: ሆሳዕና
ስልክ ቁጥር: 046 178 4632
ድርጅት: የማ/ኢ/ርዕ/መስተዳድር ጽ/ቤት
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-04
- Publishing entity: የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
- Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
- Published: May 26, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.