ሮሆቦት የመኪና የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ /ባለመብት ጌታነህ ጉርሜሳ እና በፍ/ባለዕዳ ወንደወሰን ሙሉነህ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ/15568 በ16/4/2018ዓም እና በመቁ 17949 በ8/5/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ግቢ ውስጥ ቆሞ የሚገኝ የሲቁ ኮድ 3-82610 አ.አ 10 ኩንታል የሚጭን ተሽከርካሪ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 250,000 ( ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) ሆኖ የትራክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሚያዚያ 29 ቀን 2018 ዓም በሐራጅ ለመሽጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፈ/መ/ደ/ፍ /ቤት በኮ/መ/ ቁ.17949 በቀን 07/9/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ድጋሚ ሐራጅ ሆኖ ¼ ኛ 62,500 (ስልሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ) ሆኖ የትራክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፈደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት/ ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

 

የፌዴራል ፍ/ቤት የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-12
  • Bid closing time: 11:30
  • Bid opening: 2026-06-12 11:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published: May 26, 2026
  • Posted at: 2026-05-26T10:06:38.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders