ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የፋይናንስ አማካሪ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የፋይናንስ አማካሪ አገልግሎት ግዥ
ለ2ኛ ግዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር RE-LT/HT/05/2026
- ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የፋይናንስ አማካሪ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግንቦት 20 ቀን 2018ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 09 ቀን 2018ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-10፡00 ድረስ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30-6፡00 “ሕዳሴ ቴሌኮም ኢማ” ጠመንጃ ያዥ ንግድ ባንክ አጠገብ ቴሌ ጋራዥ ግቢ ውስጥ 2ኛ ፎቅ ቢሮቁጥር 211 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት፡-
- አንድ ዋና /Original የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ፣
- አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፣
- ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በስም የታሸገ መሆን አለበት፣
- በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል። ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /C.P.O/ ብቻ ለሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 211 ሲሆን፣ ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ ቀን ሰኔ 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 211 ይሆናል።
- ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ያልተከተሉ ተጫራቾች ወዲያውኑ ከጨረታ ውድድሩ ውጪ እንደሚሆኑ እንገልጻለን።
- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0968135675 ወይም 0968271291 መጠቀም ይችላሉ።
- ሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-06-16
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-16 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Hidase Telecom Share Company
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: May 27, 2026
- Posted at: 2026-05-28T08:54:58.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.