በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ በ2018 ዓ.ም የስራ ዘመን የተለያዩ የህክምና መድኃኒቶች ሪኤጀንቶች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 003/2018 ዓ.ም

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ በ2018 ዓ.ም የስራ ዘመን የተለያዩ የህክምና መድኃኒቶች ሪኤጀንቶች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ማስያዝ የሚገባቸው የጨረታ ማስከበሪያ

1. ሎት 1 የህክምና መድኃኒቶች ሪኤጀንቶች 30,000

ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1. በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግቦ በፌዴራል ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ኤጀንሲ የምስክር ወረቀትያለው።

2. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉና የንግድ ስም ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

3. ለተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ለመሆናቸውና የግብር ከፋይ ቲንና የምዝገባ ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 400 ብር (አራት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ አጃምባ ኮንዲሚኒየም ከነማ የህዝብ መድኃኒት መሸጫ አጠገብ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 64 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10(አስር) የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት (አስራ አንድ ሰዓት) ድረስ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ቢሮ ቁጥር በመምጣት መግዛት ይቻላል።

5. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ናሙና ወይም ሳምፕል ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

6. አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ መስጠት አይችልም።

7. ገዥው በአካል የሚገዛውን እቃ እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።

8. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በኤንቨሎፕ በማሸግና ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ለእያንዳንዱ ዋጋ ከዚህ በላይ የቀረበውን ዝርዝር በማየት በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ እንዳለባቸውና ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ወይም ቢሮ ቁጥር 64 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ወይም ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ለተሸናፊዎች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለሳል።

10. አሸናፊ ተጫራቾች በሰነዱ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም ከ7ቀን በኋላ ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10% (አስር ፐርሰንት) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ አሰርተው ውል መዋዋል አለባቸው።

11. ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ቢሮ ቁጥር 48 አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ድርጅቶች በኃላፊ የተፃፈ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

አድራሻ፡- ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ አጃምባ ኮንዲሚኒየም ከነማ የህዝብ መድኃኒት መሸጫ አጠገብ ላይ ይገኛል።

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር፡ 09 20 09 03 56 መጠየቅ ይችላሉ።

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-08
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-08 12:00
  • Bid opening (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kolfe Keranio Sub City Woreda 11 Health Office
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published: May 27, 2026
  • Posted at: 2026-05-28T10:56:06.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders