ፈደንጓ የመልሶ ማልማት የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር የ2018 ዓ.ም የሂሳብ ዓመት ሂሳብ መዛግብቱን እና በዓመቱ የተከናወኑ የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችን በውጭ ኦዲተር አሰናድቶ ማቅረብ ይፈልጋል

Description

የውጭ ኦዲት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ

ፈደንጓ የመልሶ ማልማት የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር የ2018 ዓ.ም የሂሳብ ዓመት ሂሳብ መዛግብቱን እና በዓመቱ የተከናወኑ የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችን በውጭ ኦዲተር አሰናድቶ ማቅረብ ይፈልጋል።

ስለሆነም በዘርፉ የተሰማሩ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የኦዲት ድርጅቶችን (Audit firms) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

  • የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
  • የፌደራል ዋና ኦዲተር ወይም የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ (AABE) የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ የሚችሉ፣
  • በዘርፉ በቂ የሥራ ልምድ ያላቸው እና የባለሙያዎቻቸውን CV ማቅረብ የሚችሉ፣
  • በአዲሱ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ስታንዳርድ (IFRS) መሠረት ኦዲት የማድረግ ሙሉ አቅምና ልምድ ያላቸው።
  • መልካም የሙያ ስነምግባር ያለው
  • የአክሲዮን ማህበሩ ወይም የባለአክሲዮን ሰራተኛ ያልሆነ
  • በንግድ ህጉ በአንቀጽ 306 ንዑስ አንቀጽ 6 በተመለከተው መሠረት ለማህበሩ ዝምድና ወይም ቅርበት የሌለው

የማመልከቻ አቀራረብ፡-

ተጫራቾች የቴክኒክ (Technical) እና የፋይናንስ (Financial) ሰነዶቻቸውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7 የሥራ ቀናት ውስጥ ፈደንጓ የመልሶ ማልማት የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር ዋና መሥሪያ ቤት ድረስ በመምጣት ማቅረብ ይችላሉ።

አድራሻ፡ አዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 7 ሰንጋተራ ከሮያል ፕላዛ አጠገብ አራተኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር፡ 09 91 57 30 72 / 09 12 70 27 24

ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ፈደንጓ የመልሶ ማልማት የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-06-03
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7 የሥራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-06-03 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ፈደንጓ መልሶ ማልማት የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር
  • Published: May 27, 2026
  • Posted at: 2026-05-28T10:58:26.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders