የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን የተዘጋጀ የደንብ ልብስ እንዲሁም ጫማ እና ሴፍቲ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተጠቀሰውን አገልግሎት /እቃ / ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ተቁ |
የዕቃው ዓይነት |
ጨረታው የሚዘጋበት |
ጨረታው የሚከፈትበት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን /ብር/ |
||
|
ሎት 1 |
የተዘጋጀ የደንብ ልብስ |
ቀን |
ሰዓት |
ቀን |
ሰዓት |
|
|
5/10/2018 |
4:00 |
5/10/2018 |
4:30 |
|||
|
5/10/2018 |
4:00 |
5/10/2018 |
4:30 |
|||
|
ሎት 2 |
ጫማ እና ሴፍቲ |
|
|
|
|
በአጠቃላይ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% |
|
|
|
|
|
|||
በዚሁ መሠረት ከላይ ለተገለፀው ግዥ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የግዥ ዓይነት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ (Value added tax) ተመዝጋቢ መሆናቸውን፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀቶች፣ በአቅራቢነት ድረ-ገፅ (WebSite) ዝርዝር ላይ የተመዘገቡና መመዝገባቸውን የሚያሳይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችላቸው ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሚሰጥ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
1 ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በዚህ ማስታወቂያ በስተመጨረሻ በተገለጸው አድራሻ በቢሮ ቁጥር ብሎክ 3 በግንባር በመቅረብ የማይመለስ ብር 400.00 / አራት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፤
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በአጠቃለይ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የዋስትና ሰነዶች ከታወቀ ምንጭ የቀረቡ መሆን አለባቸው።
3. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ፣ ኦርጅናልና ኮፒዎችን ለየብቻው በትልቅ ፖስታ በማሸግና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ማስገባት አለባቸው፣
4. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO በማስያዝ ውል የመዋዋል ግዴታ አለባቸው፣
5. ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የለውም፤
6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃዎች ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በሎጀስቲክስና ፕሮኪዩርመንት ዳይሬክቶሬት ብሎክ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
8. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ማለትም 11ኛው ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ሰአት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፣
9. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የናሙና መረጣ ይከናወናል፡፡በናሙና መረጣ ወቅት ተጫራቹ ያቀረበው ናሙና ጥራት ዝቅተኛ ከሆነ የጨረታ ሰነዱ ሳይከፈት እንዲወስድ ይደረጋል።
10. ተጫራቾች በሚሰጡት የዕቃ ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ካላካተቱ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ተቆጥሮ ይወሰዳል።
11.በመጫረቻ ሠነዱ የቀረበው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት ጀምሮ ለ60 ቀናት የፀና ይሆናል።
12. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- 22 ማዞሪያ አውራሪስ ሆቴል አጠገብ
በስልክ ቁጥር፡-0916864568 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-06-12
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-12 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Mineral Corporation (EMC)
- Buyer address: 22 ማዞሪያ አውራሪስ ሆቴል አጠገብ
- Bid bond: በአጠቃላይ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2%
- Bid document price: 400.00 (አራት መቶ ብር)
- Published: May 29, 2026
- Posted at: 2026-05-29T07:09:07.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.