የአ/አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የታሸገ ውሃ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር AAC NCB 0011/2018 ዓ.ም

የአ/አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።

ሎት

የዕቃው ዓይነት

የናሙና መለያ

የጨረታማስከበሪያ ገንዘብ መጠን

001

1/2 የታሸገ ውሃ ግዥ

በተቋሙ ፍላጎት መሰረት

150,000

00

ስለዚህ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን እና በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው ይመልከቱ የሚል ፅሁፍ በግልጽ ማቅረብ አለባቸው፣

2. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

3. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ እና ንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

4. የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።

5. በጨረታ ስመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤

6. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም።

7. በጨረታ ሰመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታጠቀ ተመላሽ የሚሆን በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ - ዋስትና ስአዲስ አበባ ፖሲስ ተብሎ በተዘጋጀው ከባንከ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.አ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

8. ተጫራቾች ቴከኒካል ሰነዶችንና የዋጋ ማቅረቢያዎችን ፋይናንሻል ሰነዶች በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለባቸው።

9. ማንኛውንም ተጫራቾች የሚያስገባው ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ እንደ ኦሪጅናልና እንደ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረትበትን ዕቃ አይነት በትከከል መፃፍ እንዲሁም በፖስታ ላይ ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን።

10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ሲፒኦ ከቴክኒክ ሰነዶችጋር በአንድ ላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው።

11. በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን በራሳቸው ትራንስፖርት ኢ አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ግምጃ ቤት ወይም በክፍል 6 በፍላጎት መግለጫው በተጠቀሰው የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።

12. በጨረታ ሰነድ በክርስ 6 ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ በሚገለፀው መሰረት ጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው መሰረት ናሙና ማቅረብ አለበት።

13. ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙናም ሆነ አሸናፊ መሆናቸው ሲረጋገጥ ያቀርቡአቸው ዕቃዎች ተቋሙ ባወጣው ፍላጎት መግለጫ/specification/ መሰረት መሆኑን በተቋሙ የጥራት ኮሚቴ ወይም በኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ኤጀንሲ አማካኝነት የሚረጋገጥ ይሆናል።

14. ተጫራቾች አራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ ግዢ ጽ/ቤት ቢሮ ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መገዛት ይችላሉ፣

15. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 07 የስራ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በማግስቱ በ8ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ድረስ ጨረታው ከፍት ሆኖ ስለሚቆይ በተቋሙ ግዢና ፋይናንስ 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

16. በጨረታ ሰነዱ - ክፍል 2 ላይ በሚጠቀሰው ቀን ከጠዋት 4፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 5፡00 ሰዓት ሲሆን በመ/ቤቱ 5ኛ ፎቅ ትንሹ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 52 ይከፈታል፤

17. ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

18. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስ/ቁጥር 011 862-5800(011 111 0448)
የአ/አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-06
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ8ኛው ቀን ጠዋቱ 4፡30
  • Bid opening: 2026-06-06 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ8ኛው ቀን 5፡00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የአ/አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ
  • Bid bond: 150,000 ብር
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: May 29, 2026
  • Posted at: 2026-05-29T07:26:57.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders