የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ2018 ዓ.ም. የተለያዩ ሞዴል ያላቸው ያገለገሉ የመኪና ጎማ እና ባትሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የሽያጭ መስያ ቁጥር ድ/ዳ/ዩ/ሽ/ጨ/01/ 2018

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ2018 ዓ.ም የተለያዩ ሞዴል ያላቸው ያገለገሉ የመኪና ጎማ እና ባትሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የሀገር ውስጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

በዚህም መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 9 ከተጠቀሱት አድራሻዎች ለእያንዳዳቸው የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፤

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ በተ.ቁ 9 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3. የጨረታው ሳጥን በዚሁ ዕለት እና ቦታ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው አካተው ማቅረብ ያለባቸው ሰነዶች የሚከተሉት ናቸው፣

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከዚህ በታች በተገለፀው ሰንጠረዥ መሰረት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤

የእቃዎች መግለጫ

  • የተለያዩ ሞዴል ያላቸው የመኪና ጎማዎች ብዛት 311
  • 70 አምፒር የመኪና ባትሪ ብዛት 34
  • ጨረታ ማስከበሪያ መጠን 50,000.00 ብር
  • የሰነድ ሽያጩን ብር በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በሂሳብ ቁጥር 1000014248017

6. ከዚህም በተጨማሪ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋስትና የጨረታ ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት ቀን በኋላ ላሉት 28 ቀናት ዋስትናውን ሕጋዊነት የሚያረጋግጥ መሆን ይኖርበታል።

7. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ለአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የሥራ አፈፃፀም ዋስትና በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ተጫራቾች አቅርቦቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በጨረታ ሰነድ ላይ በተቀመጠው ቀን ውስጥ ማውጣት ይጠበቅባቸዋል።

8. ዩኒቨርሲቲው የተጫራቾችን ብቃት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መስፈርቶች፣ የጨረታ መመሪያዎችና ሌሎችም ተዛማጅነት ያላቸውን መረጃዎች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ያካተተ ስለሆነ በሁሉም ተሳታፊ ተጫራቾች እንዲተገበሩ ያሳስባል፤

9.ዩኒቨርሲተው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፤ ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤

  • ድሬዳዋ ዩኒርቨሲቲ አስተዳደር ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 24
  • ስልክ ቁጥር 09 37 92 24 21/ 09 15 76 20 04 - ፋክስ ቁጥር 025 112 7971/77

ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1362

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-15
  • Publishing entity: Dire Dawa University
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published: May 29, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders