ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር የ2018 ዓም በጀት ዓመት ሂሳብ ለማስመርመር የውጪ ኦዲተሮችን አወዳድሮ ውል በመግባት ማሰራት ይፈልጋል
Description
በውጪ ኦዲተሮች ሂሳብ ለማስመርመር
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር የ2018 ዓም በጀት ዓመት ሂሳብ ለማስመርመር የውጪ ኦዲተሮችን አወዳድሮ ውል በመግባት ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ እየገለጽን፤
1. ተወዳዳሪዎች በጨረታ ለመወዳደር የሚችሉ ለመሆናቸው የንግድ ፈቃድ፣ የሙያ ማረጋገጫ ሰርተፊኬትና የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመከፈላቸው ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ህጋዊ አካል የተፃፈ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ከፈቃድ ሰጪው አካል ከፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት እና ከኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
4. የ "IFRS" ሰርቲፋይድ የሆነ እና በ "IFRS" እና በGAP ኦዲት ሪፖርት ማቅረብ የሚችል።
5. ተጫራቾች ከዚህ ቀደም ከሠሩባቸው መ/ቤቶች ለሠሩበት ምስክርነት Import Export and audit ሥራ የሠራ የሚሠጡ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃዎችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች ጨረታውን 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ጠቅላላ ዋጋ ብር 30,000.00 (ሰላሣ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች የሥራውን መጠን ለማወቅ በአካል ማየት ይችላሉ።
9. ተጫራቾች ኩባንያው የሰጣቸውን የኦዲት ሥራ አጠናቀው የሚያስረክቡበትን ጊዜ በጽሁፍ አረጋግጠው ማቅረብ አለባቸው።
10. ፋይናንሻል እና ቴክኒካል በኦርጂናል እና በኮፒ እያንዳንዱ ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማሳረፍና በፖስታ በማሸግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ዋናው መ/ቤት አ.አ 7ኛ ፎቅ ማስገባት አለባቸው።
11. አሸናፊው ድርጅት በአምስት ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር መቶኛ) የውል ማስከበሪያ በማስያዝ የስምምነቱን ውል መፈረም አለበት።
12. የጨረታ መዝጊያው ሰዓት ከደረሰ እና የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
13. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
14. ጨረታው አ.አ መስቀል አደባባይ ፊንፊኔ ህንፃ ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ፋይ/ግዢ ንብ/አስ/መምሪያ 7ኛ ፎቅ የሚከፈት ይሆናል።
15. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል።
16. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ላይ ቀኑ የሥራ ቀን ከሆነ በዕለቱ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በዋናው መ/ቤት አዲስ አበባ ይከፈታል።
17. የጨረታ መዝጊያው ሰዓት ከደረሰ እና የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀረቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
18. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር-
- መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ፊንፊኔ ህንፃ 7ኛ ፎቅ
- ስልክ ቁጥር 011 552 1009 / 011- 552 1458/ ፖ.ሣ.ቁ. 9515 ፋክስ 011 551 3654
ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-06-15
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ላይ ቀኑ የሥራ ቀን ከሆነ በዕለቱ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-15 14:30
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ላይ ቀኑ የሥራ ቀን ከሆነ በዕለቱ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Wendo Trade and Investment Company
- Buyer address: መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ፊንፊኔ ህንፃ 7ኛ ፎቅ
- Bid bond: 30,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: May 29, 2026
- Posted at: 2026-05-29T08:14:25.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.