Books, manuals and publications

የማዕከላዊ ኢትጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ.ም በዩኒሴፍ በጀት የተፋጠነ የትምህርት ቤት ዝግጁነት በሃዲይሳ ቋንቋ የተዘጋጁትን የመማሪያ ማስተማሪያ መጻሕፍት ህትመትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል

Description

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ 009

የማዕከላዊ ኢትጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ.ም በዩኒሴፍ በጀት የተፋጠነ የትምህርት ቤት ዝግጁነት በሃዲይሳ ቋንቋ የተዘጋጁትን የመማሪያ ማስተማሪያ መጻሕፍት ህትመትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል።

ስለሆነም ማንኛውም በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች በውድድሩ ላይ እንዲካፈሉ እየጋበዝን በውድድሩ ላይ ለመካፈል ተጥሎ የቀረቡትን መመዘኛዎች ወይንም መስፈርቶችን ማማላት ይኖርባቸዋል፤

መስፈርት

1. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ በግብር / ከፋይነት ተመዝግበው የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣አስተማማኝ ዋስትና መስጠት የሚችል፤ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የዘመኑን የግብር ግዴታ የተወጡበትን መረጃ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

2. ተጫራቾች ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ትምህርት ቢሮ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 001 በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ፋይናንሻል እና ቴክኒካል አንዳንድ ኦርጂናል እና ኮፒ ለየብቻ ለይቶ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቢሮው ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 001 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

5. ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሚያስገቡበት ቀን ናሙና አብሮ ማቅረብ አለባቸው።

7 መ/ቤቱ በጨረታው ላይ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ - ቁጥር 046-771-06-88 መደወል ይችላሉ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ

ወራቤ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-08
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-08 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት 8፡30 ሰዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Central Ethiopia Regional Government Education Bureau
  • Bid bond: 15,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (May 29, 2026)
  • Posted at: 2026-05-29T08:27:38.000Z
← Back to all tenders