የሀላባ ሕዝብ ልማት ማህበር የ2025 ዓመት አመታዊ የገቢ እና የወጪ ሂሳብ ኦዲት ለማሠራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀላባ ሕዝብ ልማት ማህበር የ2025 ዓመት አመታዊ የገቢ እና የወጪ ሂሳብ ኦዲት ለማሠራት ይፈልጋል።
ስለዚህ የውጭ ኦዲት አገልግሎት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን በዘርፉ ብቁ የሆኑ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
የተቋሙ መረጃ
1. የተቋም ስም- የሀላባ ሕዝብ ልማት ማህበር
አድራሻ: በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ሀላባ ዞን ሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር
2 የጨረታው ርዕስ፤ የውጭ ኦዲት አገልግሎት ግዥ
3. የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
4. የጨረታ ሰነድ መሸጫ ቦታ የጨረታ ሰነዱ የሀላባ ሕዝብ ልማት ማህበር ህንጻ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት የፋይናንስና ግዥ ክፍል የጨረታ ኮሚቴ በአካል በመገኘት መግዛት ይችላል።
5. የጨረታ ማስከበሪያ ተጫራቾች ከጠቅላላው የጨረታ ዋጋ 20% በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው።
6. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ተጫራቾች፦
- በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት በሕጋዊ መንገድ የተመዘገበ እና ትክክለኛ የንግድ ፈቃድ ያለው።
- በኢትዮጵያ የሂሳብ እና ኦዲት ቦርድ (AABE) ወይም በሌላ ዓለም አቀፍ እውቅና ባለው አካል እውቅና ያገኘ።
- የTN ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የVAT ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፣ ከግብር እዳ ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያላቸው።
- ቢያንስ ለ 5 ዓመታት በውጭ ኦዲት ዘርፍ ልምድ ያለው።
- በመንግስት ተቋማት ወይም በትልልቅ ድርጅቶች ላይ ተመሳሳይ የኦዲት ሥራ ያከናወነ።
- በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከጨረታ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጋር ግንኙነት የሌለው።
7. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ
ተጫራቾች 22/9/2018 ዓ.ም የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማቅረብ የሀላባ ሕዝብ ልማት ማህበር ጽ/ቤት የፋይናንስና ግዥ ክፍል ጨረታ ኮሚቴ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. የጨረታ መክፈቻ
ጨረታው የሚከፈትበት 2/10/2018 ዓ.ም በተቋሙ የጨረታ ኮሚቴ ፊት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
9. ማሳሰቢያ
- ተቋሙ የተሻለ ጥቅም ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
- ዘግይተው የሚቀርቡ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- ማንኛውም የሐሰት ሰነድ የሚያቀርብ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይደረጋል።
የሀላባ ህዝብ ልማት ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-06-09
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ተጫራቾች 22/9/2018 ዓ.ም የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማቅረብ የሀላባ ሕዝብ ልማት ማህበር ጽ/ቤት የፋይናንስና ግዥ ክፍል ጨረታ ኮሚቴ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል
- Bid opening: 2026-06-09 17:00
- Bid opening (note): 2/10/2018 ዓ.ም
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Halaba People Development Association
- Bid bond: 20%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: May 30, 2026
- Posted at: 2026-05-30T07:54:14.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.