በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል የተለያዩ ዕቃዎችን ለ2018 በጀት ዓመት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
የእቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ፣ ጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/ቁ/06/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች ለ2018 በጀት ዓመት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡
- ሎት 1፡- አላቂ የህክምና አቅርቦቶች ግዥ
- ሎት 2፡- የኦክስጅን አቅርቦት ግዥ
- ሎት 3፤ የምግብ አቅርቦት ግዥ
- ሎት 4፡- የአጥንት ህክምና መሣሪያ ቋሚ ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልግ ተጫራች፡-
1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር ከፍሎ ፍቃዱን ያደሰ፤
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ወይም የሙያ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለውና፣ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
3. የአቅራቢነት ማስረጃ ያለው፤
4. ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ስለ ግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚች፤ መሆን ይኖርባቸዋል።
5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሣተፍ የጨረታ ማስከበሪያ
- ሎት 1፡- አላቂ የህከምና አቅርቦቶች ግዥ 50000.00 ብር
- ሎት 2፡- የኦክስጅን አቅርቦት ግዥ 100000.00 ብር
- ሎት 3 የምግብ አቅርቦት ግዥ 100000.00 ብር
- ሎት 4- የአጥንት ህክምና መሣሪያ ቋሚ ዕቃዎች ግዥ 350000.00 ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO)፤ ወይም ጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
6. ተጫራቾች የናሙናዎቻቸውን ሰነድ ሲገዙ የተሰጣቸው መለያ ኮዳቸውን ሰጥተው ማቅረብ አለባቸው። በተጨማሪም ለአንድ የአቅርቦት ዓይነት አንድ ናሙና ብቻ ማቅረብ አለባቸው።(ለምግብ አቅርቦት)።
7. አሸናፊ ተጫራቾች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የእቃ ክምችት (የራሱ ስቶክ) ያለውና፤ እቃዎቹን በራሱ ማጓጓዣ (ወጪ) እስከ ሆስፒታሉ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ አምጥቶ እና በራሱ ወጪ አውርዶ ማስረከብ አለበት
8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ሙሉ መረጃቸውን እና፤ ኮፒ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ለመግዛት መምጣት ይኖርባቸዋል፤ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋት 2፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት በሆስፒታሉ ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር አዲስ (በመኪና መግቢያ በር ገብቶ ወደ ግራ እጥፍ ብለው) በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ የሎት ቁጥሩ፤ ሰነድ ሲገዙ የተሰጣቸው መለያ ኮድ ፅፈው፣ የድርጅታቸው ህጋዊ ማህተም መተው፤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከሎት 1 እስከ ሎት 3 ያሉት ጨረታቸው አንድ (1) ኤንቨሎፕ ነው። እንዲሁም ሎት 4 የአጥንት ህከምና መሣሪያ ቋሚ ዕቃዎች ግዥ ጨረታቸው ሁለት (2) ኤንቨሎፕ ሲሆን (ሎት 4 በአራት ፖስታ በሁለት ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ) ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ለየብቻ አሽገው፤ ኦርጅናል እና ኮፒ ለይተው ማስገባት ይኖርባችኋል።
10. ጨረታው 10 ቀናት የአየር ላይ ቆይታውን እንዳጠናቀቀ በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
11. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸው ሆስፒታላችን በሰጠው መሙያ ቅጽ ብቻ ሞምላት ይኖርባችኋል፤ ማንኛውም ስርዝ ድልዝ፣ ማህተም ያልተደረገበት የቀረበ ዋጋ፣ በሆስፒታሉ ዋጋ መሙያ ቅጽ ያልተሞላ ዋጋ ተቀባይነት የለውም። ከጨረታው ውጪ ይደረጋል።
12. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በአራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ከዮሐንስ ቤ/ክ 500 ሜትር አለፍ ብሎ እንገኛለን።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 111 2056 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-06-11
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው 10 ቀናት የአየር ላይ ቆይታውን እንዳጠናቀቀ በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-11 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው 10 ቀናት የአየር ላይ ቆይታውን እንዳጠናቀቀ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ras Desta Damtew Memorial Hospital
- Buyer address: ከፒያሳ ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ከዮሐንስ ቤ/ክ 500 ሜትር አለፍ ብሎ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: May 30, 2026
- Posted at: 2026-05-30T08:05:55.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.