የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ያገለገሉ የአስፋልት በርሜሎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ከዚህ በታች በሰንጠረዥ  የተዘረዘሩትን ያገለገሉ የአስፋልት በርሜሎች በተቀመጠላቸው መነሻ ዋጋ መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ/ቁ

የንብረቱ ዓይነት

ኪያ

ብዛት

የአንዱ ዋጋ

ምርመራ

1

ክዳን ያለው ባዶ የአስፋልት በርሜል

በቁጥር

200

 

ለተጫራቾች ዋጋን በተመለከተ መወዳደር የሚቻለው በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተዘረዘሩትን የተናጠል ዋጋ በመሙላት ውጤቱ የሚገለፀው በጥቅል (በድምር) ውጤት መሆኑ ይታወቅ፡፡

2

ክዳን የሌለው ባዶ የአስፋልት በርሜል

በቁጥር

2740

 

                                          ድምር (ጥቅል ዋጋ)

 

ስለሆነም

1ኛ. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ 300.00 (ሦስት መቶ) ብር በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000322267979 ገቢ በማድረግ ድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ቢሮ ግዥ ክፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይኖርባቸዋል።

2ኛ.ተጫራቾች ከጨረታ ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ብቻ ተጫራቾች የሚገዙበትን ጨረታ ዋጋ ስማቸውን ስልክ ቁጥራቸውን በግልጽ በመፈረም ማስቀመጥ አለባቸው

3ኛ. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ስዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ባለው ጊዜ ውስጥ ያገለገሉ በርሜሎችን በድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት (በስፍራው) ተገኝተው መመልከት ይችላሉ።

4ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) ብር በባንክ ሲፒኦ ወይም ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል

5ኛ. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አሰራ አምስት) የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ድሬድዋ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

6ኛ. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

7ኛ. አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው ከከፈሉ በኋላ ንብረቱን በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ የማንሣት ግዴታ አለባቸው

ማሳሰቢያ፡-መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

ስልክ ቁጥር 025111-13-13/0927636126/0919008017

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-17
  • Publishing entity: Ethiopian Roads Administration Dire Dawa Road Maintenance District
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: May 30, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders