አማራ ልማት ማህበር /አልማ/ የሀይል መጠባበቂያ እና መቆጣጠሪያ ባትሪ መግዛት ይፈልጋል

Description

የሀይል መጠባበቂያ እና መቆጣጠሪያ ባትሪ ግዥ በድጋሚ

የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

አማራ ልማት ማህበር /አልማ/ የክልሉን ህዝብና ልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት በማንቀሳቀስ በትምህርት፣በጤና እና በስራ እድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ ማህበራዊ ተጠቃሚነት አስተዎጾኦ በማድረግ ተልእኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው። በመሆኑም ማህበሩ ለአገልግሎት የሚውሉ ብቁና መስፈርቱን የሚያሟሉ አቅራቢዎች /Eligible and qualified Suppliers to Submit bids for the Supply, Delivery, and Warranty Support of Six /6/ Lead-Acid Batteries to be used for power Bacup Applications/ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁም መሰረት

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin no ያላቸው
  2. የግዥ መጠን 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ NAI ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  3. በመንግስት ግዥ በአዲሱ አቅራቢዎች ዝርዝር መረጃ ላይ ማለት(https://wwwegp.ppa.gov.et) መመዝገባቸው የሚችሉ
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር / በመክፈል አዲስ አበባ በሚገኘው አልማ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 203 ማግኘት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፤
  7. የሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ ከጨረታ ውጪ ያደርጋል።
  8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዶክመንት ላይ ያለምንም ስርዝ ድልዝ በመሙላት አንድ ወጥ በሆነ ኢንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው፤
  9. የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት አዲስ አበባ አልማ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 203 መግዛት የሚቻል ሲሆን፤ የጨረታው ማወዳደሪያ ሰነድ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ የፋይናንስ ለብቻ የቴክኒክ ለብቻ በማያያዝ በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ9፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል። ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አዲስ አበባ ቦሌ ማተሚያ ቤት ጎን አልማ ህንፃ 2ኛ ቢሮ ቁጥር 203 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በሰስልክ ቁጥር 011 551 2528 /በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 ሺ ሆነን እንደ አንድ አንድ ሆነን እንደ ሺ

www.ada.org.et 

አዲስ አበባ-Addis Ababa ስልክ Tele፡ +251 11 551 7886

ፋክስ Fax: +251 11 551 7795 e-mail: ada.liaison@ethionet.et/ada.hq@ethionet.et/


Tender details

  • Deadline: 2026-06-11
  • Publishing entity: Amhara Development Association (ADA)
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: May 31, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders