ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ከዕዳና ዕገዳ ነፃ የሆኑ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች፤ የተሽከርካሪ ዕቃዎች እና ሌሎች ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የተጎዱ ተሽከርካሪዎችና የተሽከርካሪዎች ቅሪት አካላት እና

ሌሎች ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ጨረታ

የጨረታ ቁጥር 06/26

ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ከዕዳና ዕገዳ ነፃ የሆኑ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች፤ የተሽከርካሪ ዕቃዎች እና ሌሎች ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች ከግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ቅዕ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች ንብረቶቹን ከግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ድረስ ከሃና ማርያም ወደ ቃሊቲ አደባባይ በሚወስደው ቀለበት መንገድ ከቻይና ጠጠር መፍጫ ፊት ለፊት በስተግራ በኩል የአጠና መሸጫ አጠገብ ከሚገኘው የኩባንያው የንብረት ማከማቻ መጋዘን ውስጥ በአካል ተገኝተው መመልከት ይችላሉ።

3. የጨረታ መነሻ ዋጋው 15% ተ.እ.ታ ያላካተተ ወይም ያልጨመረ መሆኑን እየገለፅን ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ተ.እ.ታ ሳይጨምሩ በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) ወይም በእንግሊዝኛ NATIONAL INSURANCE CO. OF ETHIOPIA (S.C.) ስም በማንኛውም ባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ጋር በኤንቨሎፕ በማሸግ ከግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ላንቻ ባቡር ጣቢያ ፊት ለፊት ዘፍኮ ሕንፃ በሚገኘው በዋናው መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 8 በሚገኘው የሰው ሀብትና ፋሲሊቲ ሥራ አመራር መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

4. ጨረታው ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ ጠዋት በ4፡30 ሰዓት ላይ ከሃና ማርያም ወደ ቃሊቲ አደባባይ በሚወስደው ቀለበት መንገድ ከቻይና ጠጠር መፍጫ ፊት ለፊት በስተግራ በኩል የአጠና መሸጫ አጠገብ ከሚገኘው የኩባንያው የንብረት ማከማቻ ግቢ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ. ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።

ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

ስልክ 011-470-5378 / 011-466-1129


Tender details

  • Deadline: 2026-06-13
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-13 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: National Ethiopian Insurance Company
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: May 31, 2026
  • Posted at: 2026-06-02T10:56:01.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders