ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ. የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች እና አዲስ አበባ ሪከቨሪ የሚገኙ የተሽከርካሪ ቅሪት አካላት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ

BUNNA INSURANCE COMPANY (S.C)

የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች እና አዲስ አበባ ሪከቨሪ የሚገኙ የተሽከርካሪ ቅሪት አካላት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተሽከርካሪዎቹንና የተሽከርካሪ አካላትን መግዛት ለሚፈልጉ ሳር ቤት ወይም አፍሪካ ህብረት ጀርባ በሚገኘው የኩባንያችን ዋና መ/ቤት ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ወይንም ቃሊቲ  የኩባንያችን ሪከቨሪ ግቢ በመገኘት የተዘጋጀውን ሰነድ በማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች የሚገዙበት ዋጋ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሠረት በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ እስከ ሰኔ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ገቢ በማድረግ መጫረት ይችላሉ።

ማሳሰቢያ

  • ተጫራቾች ንብረቾችን እና ተሽከርካሪዎችን ቃለቲ ሸዋ ዳቦ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው ሪከቨሪ ግቢ ውስጥ ከግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 05 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
  • ጨረታው ሰኔ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡30 ሰዓት በኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት የተገኙ ተጫራች ወይንም ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል።
  •  ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
  • ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት የመነሻ ዋጋውን 15% (አስራ አምስት በመቶ) በቡና ኢንሹራንስ ኢማ ወይም Bunna Insurance S.C ስም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያው ከብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) ማነስ የለበትም።
  •  ከቀረጥ ነፃ ከሆኑት ተሽከርካሪዎች በስተቀር በሌሎች  ተሽከርካሪዎች የተሽከርካሪ አካላት ከጨረታ በፊት አመታዊ የተሽከርካሪ ግብር እና ቅጣት ቢኖር በሻጭ የሚሸፍን ሲሆን ከዚህ ወጪ ያለ ዕዳ ካለ በኩባንያው ይሸፈናል:: በጨረታው ለተካተቱ ንብረቶች ከጨረታው በኋላ ያሉትን ማናቸውም ወጪዎች ገዥው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል።
  • የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፋበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላሉ።
  •  አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባለው 10 የሥራ ቀን ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ንብረቶቹን ካልተረከቡ የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል።

ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ

ሳር ቤት ወይም አፍሪካ ህብረት

ጀርባ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ

911-99-31-15/0114626090 ሪከቨሪ

011-1-26-31-46/011-1-26-28-61


Tender details

  • Deadline: 2026-06-13
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid opening: 2026-06-13 09:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bunna Insurance S.C.
  • Buyer TIN: 0038530762
  • Buyer address: ሳር ቤት ወይም አፍሪካ ህብረት ጀርባ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ
  • Bid bond: 15%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 31, 2026
  • Posted at: 2026-06-02T11:06:24.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders