Disposal, scrap and surplus sales

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መቱ ሪጅን ንብረት የሆኑ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/ንአ/ገጨ-008/2018

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መቱ ሪጅን ንብረት የሆኑ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ቁጥር

የዕቃው ዓይነት

የሚገኝበት ቦታ

ኪያ

ብዛት

የጨረታ ማስከበሪያ (CPO)

የጨረታው መዝጊያ ቀን

የጨረታው መክፈቻ ቀን

ሎት 1

ትልቁ ጎማ ባለ ክር 12.00.20

 

በቁጥር

46

5736.00

ሰኔ 01/2018 . 800 PM

ሰኔ 01/2018 . 830 PM

ትንሹ ጎማ ባለ ክር 7.50.16

በቁጥር

190

ትንሹ ጎማ ባለ ሽቦ 7.50.16

በቁጥር

144

ባትሪ70A

በቁጥር

10

264.00

ባትሪ60A

በቁጥር

5

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ገለሰብ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1. ተጫራቾች ዝርዘር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በድርጅታችን አካውንት ቁጥር (EU Account No, 1000254144127) የማይመለስ ለሎት-1 ብር 500 /አምስት መቶ/ ገቢ በማድረግ ዘወትር በሥራ ሰዓት መቱ ሪጀን ቢሮ ሕንፃ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመቱ ሪጅን ቢሮ 2ኛ ፎቅ በመምጣት የሚወገዱትን ንብረቶች ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ገዝተው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 02፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት፡ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Security) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ስማቸውን እና ጨረታ ቁጥሩን በመገለፅ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከቀኑ 08፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጠቀሰ አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመቱ ሪጅን ህንፃ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮ ይከፈታል።

6. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 047 141 4620 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ(አማራጭ) ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መቱ ሪጅን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-08
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-06-08 14:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ethiopian Electric Utility
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jun 01, 2026)
  • Posted at: 2026-06-02T11:38:53.000Z
← Back to all tenders