በወላይታ ዞን የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት ሚስትቡሽ መኪና፣ የተለያዩ ሞተር ሳይክሎች፣ የቧንቧ ብረቶች፣ የእርሻ መሳሪያዎች፣ ፕላስቲኮች፣ ቆራሌ ብረቶችና ቆርቆሮዎች፣ አሮጌ ጎማዎች፣ የውሃ ፓምፕ፣ ጀነሬተር፣ ትሪድል ፓምፕ፣ ብረታ ብረቶች እና ሌሎች ዕቃዎችን በግልጽ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሎ ንብረቶችን ለመሸጥ የወጣ
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

በወላይታ ዞን የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት በወረዳው የሚገኙ በተለያዩ ጊዜያት በግዥ፣ በዕርዳታና በስጦታ ያገኗቸውን ሚስትቡሽ መኪና የተለያዩ ሞተር ሳይክሎች፣ የቧንቧ ብረቶች፣ የእርሻ መሳሪያዎች፣ ፕላስቲኮች፣ ቆራሌ ብረቶችና ቆርቆሮዎች፣ አሮጌ ጎማዎች፣ የውሃ ፓምፕ፣ጀኔረቴር፣ ትሪድል ፓምፕ፣ ብረታ ብረቶች እና ሌሎች ዕቃዎችን በግልጽ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፤

ማንነቱን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ እና የጨረታ ሰነድ የገዙበት ደረሰኝ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከላይ የተገለጹ ያገለገሉ የመንግስት ንብረቶችን ዝርዝር የያዘውን የመወዳደሪያ ሰነድ ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በአካውንት ቁጥር 1000669192375 የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ /በማስገባት የባንክ ስሊፑን ይዘው ቢሮ ቁጥር 2 በመሄድ ሠነድ መግዛት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20% (ሃያ በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ደረሰኝ ቀደም ብሎ ገቢ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ15 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ሌሎች ታዛቢዎች በተገኙበት በሶዶ ዙ/ወ/ዋና አስ/ ጽ/ ቤት ግቢ ውስጥ ባለው አዳራሽ በግልጽ የሚካሄድ ይሆናል።

4. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ እንደተረጋገጠ ያሸነፈበትን ዋጋ ሶዶ ዙ/ወ/ገቢዎች ጽ/ቤት በአካውንት ቁጥር 1000669192375 ሙሉ በሙሉ ገቢ ሲያደርግ ያሸነፈውን ንብረት ወዲያውኑ ይረከባል፡፡ ሌሎች ዝርዝር ሂደቶች በጨረታ ሰነድ የሚካተቱ ይሆናል።

5. አሸናፊ በሆኑበት በርካታ ያገለገሉ የተለያዩ ንብረቶች፣ሞተር ብስክሌቶች እና መኪና ሽያጭ በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ስምምነት ውል ለመግባት ፍቃደኛ ካልሆኑ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።

6. የተሽከርካሪዎችን የስም ዝውውርና ህግ የሚጠይቃቸውን ማንኛውንም ክፍያዎች (ወጪዎች) አሸናፊው የሚሸፍን ይሆናል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት ዕለት ጀምሮ ለጨረታ የቀረቡ ያገለገሉ ንብረቶች የሶዶ ዙ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ንብረት መጋዘን ቢሮ ቁጥር 5 በመገኘት በስራ ሰዓት ማየት ይችላሉ።

8. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046-180-6026 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።
የወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-16
  • Publishing entity: Wolaita Zone Sodo City Finance and Economic Development Office
  • Bid bond: 20%
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Jun 01, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders