እድገት ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ለሚሰራቸው ስራዎች 1ኛ. ሎደር ማሸን፣ ሻወር ትራክ፣ ሞባይል ክሬን፣ ቢትመን ግሬድ 60/70፣ የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫና ጎማ፣ የህንጻ መሳሪያ፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ የተፈጨ ጠጠር በሜ/ኩብ፣ የግንባታ ድንጋይ በሜትር ኩብ እና አሸዋ በሜትር ኩብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018

እድገት ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ለሚሰራቸው ስራዎች 1ኛ.ሎደር ማሸን፣ ሻወር ትራክ፣ ሞባይል ክሬን፣ ቢትመን ግሬድ 60/70 ፣የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫና ጎማ፣ የህንጻ መሳሪያ፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ የተፈጨ ጠጠር በሜ/ኩብ፣ የግንባታ ድንጋይ በሜትር ኩብ እና አሸዋ በሜትር ኩብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1. ተጫራቾች ህጋዊና የታደሠ የንግድ ወይም የስራ ፈቃድ ያላቸው።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡

3. የግዥ መጠን ከብር 700,000 በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የሚገዙ ሎደር ማሸን፣ሻወር ትራክ፣ሞባይል ክሬን፣ ቢትመን ግሬድ 60/70፣የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫና ጎማ፣ የህንጻ መሳሪያ፣የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ የተፈጨ ጠጠር፣የግንባታ ድንጋይ እና አሸዋ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሠነዱ ማገኘት ይቻላል፡፡

6. ሎደር ማሸን፣ ሻወር ትራክ፣ ሞባይል ክሬን፣ ቢትመን፣ የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫና ጎማ፣የህንጻ መሳሪያ፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ፣ የተፈጨ ጠጠር የግንባታ ድንጋይ እና አሸዋ ብር ወይም እቃ ጠቅላላ ዋጋ 2% ከነቫቱ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

7. ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ግዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ 30 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡

8. የውጭ ሀገር ገንዘብ ምንዛሬ ተመን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኩል ለውጥ ከተደረገ በጨረታ ሰነድ ላይ የተሞላው ዋጋ የማይቀየር ወይም የዋጋ ማሻሻያ ተቋራጩ የማያደርግ መሆኑን።

9. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ ማለትም ለሎደር ማሸን፣ለሻወር ትራክ መኪና፣ሞባይል ክሬን የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር /ለቢትመን ግሬድ 60/70 የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ለተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫ እና ጎማ የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/፣ለህንጻ መሳሪያ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/፣ ለሰራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ የተፈጨ ጠጠር፣የግንባታ ድንጋይ እና አሸዋ የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/፣በመክፈል እድገት ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ማገኘት ይቻላል፡፡

10. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሣቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ እድገት ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሠዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሁሉም ጨረታዎች ለተከታታይ 16 ቀን እስከ ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባ ይኖርባቸዋል። በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ16ኛው ቀን 4፡30 ይከፈታል።

11. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ እስከ 16ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርበታል፤ በዚሁ ሰአት ይታሽጋል። የጨረታ ሳጥን ከታሸገ እና ጨረታ መከፈት ከጀመረ ቦኋላ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ተቀባይነት የሌለውና ተጫራቹን ከጨረታ ውድድር ውጭ መ/ቤቱ የሚያደርግ መሆኑን እንገልጻለን።

12. ማንኛውም ተጫራቾች ያቀረበው የጨረታ ሰነድ ፖስታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ሲ.ፒ.ኦ የሌለው ከሆነ በጨረታ ሰነዱ ላይ የሞላው ዋጋ የማይነበብና ተጫራቹም ከጨረታ ውድድር ውጭ የሚሆን መሆኑን እናሳውቃለን።

13. ማንኛውም ተጫራቾች ዋጋ መሙላት የሚችለው መ/ቤቱ ባቀረበለት የዋጋ መሙያ ሰነድ ብቻ ሲሆን በሌላ ወይም በራሱ የዋጋ መሙያ ሞልቶ ቢያቀርብ ተጫራቹን መ/ቤቱ ከጨረታ ውድድር ውጭ የሚደርግ እና በሁለት ዋጋ መሙያ ሞልቶ ያቀረበውን ተጫራች መ/ቤቱ በህግ የሚጠይቅ መሆኑን እናሳውቃለን።

14. ጨረታው ለሁሉም እቃዎች የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእድገት ጠቅለላ ስራ ተቋራጭ መ/ቤት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ይከፈታል፤ የሚከፈትበት ቀን የበዓላት ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ካልተገኙ ተቋራጩ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. አሸናፊው ድርጅትያሸነፈበትንእቃ፣ተሽከርካሪ እና ማሸነሪ ደሴ ከተማ እድገት ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ መ/ቤት ድረስ በራሱ ማጓጓዥ የማስጫኛ እና ማውረጃ ወጭን ሸፍኖ ማቅረብ ይኖርበታል።

16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

17. አሸናፊው ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ለውል ማስከበሪያ የሚሆን 10% የሚያስይዙ መሆኑን።

18. በጨረታ ለመሣተፍ የሚፈልጉና ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር ቁጥር 033 311 23 28/23 29/23 27/23 26 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

አድራሻ ፡- ዴሴ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ህንጻ 3ኛ ፎቅ

እድገት ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-17
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-17 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Edget General Contractor
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published: Jun 02, 2026
  • Posted at: 2026-06-03T08:16:02.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders