በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ በአዳማ ቅርንጫፍ የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ - የግ/ው/ሽ/ሜ/አ/ዘ/ግጨ/ሸ04/2018 

በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ በአዳማ ቅርንጫፍ የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁና፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፤ የንግድ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክርነት ወረቀት(ክሊራንስ) ኮፒ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

2. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ በባንክ የተመሰከረ CPO በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፓሬሽን የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ ስም ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ጋር በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ለ30 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል።

3. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡የዕጣን ምርቶች ሽያጭ ተጫራቹ በሚሰጠው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይጨመራል።

4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከመጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ሀሙስ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10፡30 እንዲሁም ዓርብ፤ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-5፡30 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30- 10:30 በዘርፍ ጽ/ቤት ቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት በኢግሥኮ የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልገሎት ዘርፍ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 አንዲሁም በአዳማ ከተማ መብራት ኃይል ንግድ ምክር ቤት ጎን አዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

5. ጨረታው ሰኔ 05 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ሰኔ 05 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መ/ቤት በግብርና ውጤቶች እና ሜካናይዜሽን አገልግሎት በዘርፉ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 110ና በኮርፖሬሽኑ አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል።

6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከቀረበው ዝርዝር ምርቶች ውስጥ በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይቻላል።

7. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፤

8. ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ

አዲስ አበባ 011470-84-75/0116-66-23-90

አዳማ 0221 11-2 1-22/0221-11-31-56

በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-12
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-06-12 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ
  • Bid bond: ከ2% ያላነሰ
  • Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 02, 2026
  • Posted at: 2026-06-03T08:29:47.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders