ሪፕል ኢፈክት ኢትዮጵያ ከስታር ባክስ ፋዉንዴሽን (Starbucks Foundation) ጋር በመተባበር በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በንሳ ወረዳ የሚገኙ አነሰተኛ የመሬት ይዞታ ያላቸው ሴት አርሶ አደሮችን አቅም ማጎልበት (Resilient and Empowered women and girls project) ለተባለዉ ፕሮጀክት ለተጠቃሚ አርሶ አደሮች የሚሆን የሽግግር የንብ ቄፎ(Transitional top b

Description

ድጋሜ የወጣ የጨረታ ማስታወቅያ

የኬንያ ቶፕ ባር(Transitional top bar hive) ግዢ ጨረታ

ሪፕል ኢፈክት ኢትዮጵያ (በቀድሞ ስሙ ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ) እ ኤ አ ከ 2006 ጀምሮ በኢትዮጵያ በዘላቂ ግብርና፣እንሰሳት አያያዝ ፣ ተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ፣የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ቅነሳ እና መሰል የልማት ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው።

በአሁኑ ሰዓት ድርጅቱ ከስታር ባክስ ፋዉንዴሽን (Starbucks Foundation) ጋር በመተባበር በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በንሳ ወረዳ የሚገኙ አነሰተኛ የመሬት ይዞታ ያላቸው ሴት አርሶ አደሮችን አቅም ማጎልበት (Resilent amd Empowerd women and girls project) ለተባለዉ ፕሮጀክት ለተጠቃም አርሶ አደሮች የሚሆን የሽግግር የንብ ቄፎ(Transitional top bar hive) ህጋዊ ፈቃድ ካላቸውና በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በዘርፉ የተሰማራችሁና ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች የጨረታ ሰነዶቻችሁን ከታች በተጠቀሰው የድርጅቱ አድራሻ በማስገባት እንድትወዳድሩ ይጋብዛል።

1. የጨረታ መደብ /Lot/:- የሽግግር የንብ ቄፎ(Transitional Top Bar Hive)

S/N

የዕቃዉ ዓይነት

መለክያ

ዛት

የኬንያ ቶፕ ባር ለማዘጋጀት መሟላት ያለበት ( እስፔስፊኬሽን) እንደሚከተለው ነው::

1

የኬንያ ቶፕ ባር (Transitional Top Bar Hives)

በቁጥር

150

1. የቀፎው ምርት ከደረቀ ዋንዛ ወይም ዝግባ ሊሠራ ይገባል፣

2. የቀፎው ምርት የሚሰራበት ጣውላ በምንም ዓይነት ተዋሕስያን ያልተጠቃ መሆን አለበት፣ የኬኒያ ቶፕ ባር

3. ጣውላው ያልተሰነጣጠቀ ቋር የሌለበትና ምንም ዓይነት ቀዳዳ የማይታይበት መሆን ይኖርበታል::

4. የቀፎው ምርት ውጫዊ ልኬት

  • ርዝመት---94 .ሜትር
  • ስፋት---44 .ሜትር
  • ስፋት ከታች---25 .ሜትር
  • የጎን ስፋት---28.5 .ሜትር

5. የቀፎው ምርት ውስጣዊ ልኬት

  • ርዝመት---90 .ሜትር
  • ስፋት ከላይ---40 .ሜትር
  • ስፋት ከታች---21 .ሜትር
  • ጥልቀት---26.5 .ሜትር

6. ቀፎው ላይ የሚደረደሩት ርብራቦች ልኬት

  • ርዝመት---44 .ሜትር
  • ስፋት ከላይ---3.2 .ሜትር
  • ስፋት ከታች---0.9 እስከ 1 .ሜትር( ሼፕ ከወጣለት ቦታ ላይ)
  • የእንጨቱ ውፍረት---2 .ሜትር

7. የንቦች መግቢያና መውጫ በር ልኬት

  • ርዝመት---10 .ሜትር
  • ጥልቀት---1.5 .ሜትር

8. የቀፎው ኪዳን ከማይዝግ ልሙጥ ቆርቆሮ ሆኖ ልኬታው 118×63 .ሜትር በመቁረጥ በአራቱም ጠርዞች 4 .ሜትር ገባ ብሎ የታጠፈና በተዘጋጀው እንጨት ላይ የሚያያዝ መሆን አለበት::

9. የቀፎው ኪዳን ልኬት

  • 110x55 .ሜትር

10. የንቦች ማኮብኮቢያ

  • ርዝመት---20 .ሜትር
  • ስፋት---10 .ሜትር
  • ውፍረት---2 .ሜትር ተዘጋጅቶ በማጠፊያ ይያያዛል::

11. እያንዳንዱ የቀፎ ምርት 28 ርብራቦች ያስፈልጉታል፣

12. የቀፎው ምርት ከደማቅ ቢጫ የፕላስቲክ ቀለም የተቀባ መሆን አለበት፣ በካዲስኮ ምርት የቀለም ቁጥር 172 ተመራጭ ነው::

13. የቀፎው ውስጣዊ አካል ሙሉ ለሙሉ በደንብ ለስልሶ መዘጋጀት አለበት፣

14. የንቦች መግቢያ ቀዳዳ በአረንጓዴ ቀለም ይቀባል፣

የጨረታ መስፈርት

1. ህጋዊ ሰነዶች:-

  • ለ2018 ዓ/ም የታደሰ የንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ሴርትፍኬት፣
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN NUMBER)፤
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባና የምስክር ወርቀት፤
  • የግብር ክልራንስ ስርቴፍኬት፤
  • የተለያዩ የድጋፍ ስነዶች እና ሴርትፍከቶች

2. ተጫራቾች የጨረታ ስነዶቻቸውን በፖስታ አሽገው በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረብያቸው ላይ ዋጋው ጸንቶ የሚቆይበትን ግዜና ቫት ማካተትና አለማካተቱን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል።

4. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረብያቸው ላይ የትራንስፖርት ወጪን(Transportation Cost)ማካተት ይጠበቅባቸዋል።

5. የአቅራብ ድርጅት ለእቃዉ የስድስት ወር ዋስትና (Warranty) ለመስጠት ፍቃደኛ የሆነ/መስጠት የምችል።

6. ተጨራቾች በተጠየቁ ጊዜ የተወዳደሩበትን ቁሳቁስ ናሙና(Sample) ለማሳየት ወይም ለማቅረብ ፈቃደኛ መሆን ይኖርባቸዋል።

7. የተበላሹ ወይም ደረጃቸውን ያልጠበቁ ቀፎዎች በአቅራቢው ዋጋ ይተካሉ።

8. የጨረታ ማስገቢያ ጊዜ ከግንቦት 24, 2018 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5(አምስት) የስራ ቀናት ስሆን፤ ጨረታዉ የምከፈትበት ቀን ሰኔ 02,2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00 ስዓት በፐሮጄክቱ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ወክሎቻቸዉ በተገኙበት ይሆናል።

9. ሪፕል ኢፌክት ኢትዮጵያ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ጨረታ አሽናፍ የሚለየው ከላይ የተጠቀሱትን ህጋዊ ስነዶችን እና ለእቃዉ ዝቅተኛ ዋጋ(Least unit price)ያቀረበ ተጫራች ይሆናል።

11. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ አድራሻ፤

  • ሪፕል ኢፌክት ኢንተርናሸናል፤ በሲዳማ ክልል ሚስራቃዊ ዞን፣ በንሳ ዳዬ ፕሮጄክት ቢሮ፣ ዳዬ ከተማ የበንሳ አከባበ ከፍተኛ ፍ/ቤት 50 ሜትር ገባ ብሎ ወይም ዳዬ ከተማ መለስተኛ ት/ቤት(ዳሞ ት/ቤት) ትንሸ ከፍ ብሎ ነዉ።
  • ሪፕል ኢፈክት ኢንተርናሽናል ካሳንችስ ወረዳ 08 ከእሊለ ሆተል ቀጥሎ SA ሕንጻ(ህብረት ባንክ ያለበት ) ፣ 7ተኛ ፎቅ ስልክ ቁጥር (+251)-9-23-01-51-75 ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ።

12 ለተጨማር መረጃ ከታች ባለው ስልክ ይደዉሉ::

  • አቶ ባንጃ ባርጋና፣ ስልክ ቁጥር 0909 887 698 እና
  • አቶ እጅጉ ሮማ፤ ስልክ ቁጥር 0916 361 183

Tender details

  • Deadline: 2026-06-09
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ከግንቦት 24, 2018 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5(አምስት) የስራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-06-09 10:00
  • Bid opening (note): ሰኔ 02,2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ripple Effect Ethiopia
  • Published: Jun 03, 2026
  • Posted at: 2026-06-03T10:53:17.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders