ዓባይ ሕትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ወረቀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አሕየወፓ-ሽ04/2018

ዓባይ የህትመትና የወረቀት ፓኬጅንግ ፋብሪካ ንፁህ 250ግራም እና 180 ግራም የውጭ ማኔላ ወረቀት በተለያየ ከለር እና በተለያየ ሳይዝ ማለትም 61 * 86 እና 70 *100 ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ጊዜ ብቻ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች መሰረት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።

1. መወዳደር የሚችል ማንኛውም ድርጅት፣ ተቋም ወይም ግለሰብ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና (TIN) ያላቸው መሆን አለባቸው፤

2. ንፁህ ማኒላ ወረቀት የሚገኝበት ቦታ ማየት የፈለጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታዉ መዝጊያ ቀን ድረስ በአካል በመቅረብ ማየት ይችላሉ።

3. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ፤ የተጫራቾች መመሪያ፤ የዉል ረቂቅ፤ የዋጋ መሙያ ፎርምና ቴክኒክ መግለጫ ያያዘዉን የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዓባይ ሕትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ኢንዱስትሪ መንደር ከጣና ሞባይል አከባቢ ከሚገኘዉ ከፋብሪካዉ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ወይም አዲስ አበባ 4 ኪሎ አማራ ልማት ማህበር አዲሱ ሀንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 219 ከሚገኘዉ ከፋብሪካዉ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000281546078 ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን የባንክ ደረሰኝ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ተጨማሪ እሴት ታከስን ጨምሮ የጠቅላላ ዋጋዉን 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድረገዉ ማቅረብ አለባቸዉ:: ሆኖም ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ስሌት መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከ500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የሚያሲዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠኑ 500,000.00 ብር ብቻ ማስያዝ ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ እና የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ እስከ 30 (ሰላሳ) ቀናት ድረስ ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት እንዲሁም የጨረታ ዋጋ በውሉ የፀና መሆን አለበት።

6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በፋብሪካ ባህርዳር ግዥና ሎጅስቲክስ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታዉ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ሰኔ 11/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤

7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባህርዳር ግዥና ሎጅስቲክስ መምሪያ ቢሮ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8:30 ሰዓት ይከፈታል:: በመሆኑም ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል።

8. ፋብሪካዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

9. በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከፋብሪካዉ ግዥና ሎጅስቲክስ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 0583218865/0942050954/ 0911709127 በመደወል ማግኘት ይቻላል።

ዓባይ ሕትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ባህር ዳር


Tender details

  • Deadline: 2026-06-18
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-06-18 14:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Abay Printing & Paper Packaging P.L.C.
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 300 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 03, 2026
  • Posted at: 2026-06-03T12:15:03.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders