ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ውል ወስዶ እየገነባው ላለው ለደሴ አሚኮ ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮ መካኒካል (AC System) አቅርቦት እና ገጠማ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 51/2018

ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ውል ወስዶ እየገነባው ላለው ለደሴ አሚኮ ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮ መካኒካል (AC System) አቅርቦት እና ገጠማ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ስመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾቾ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤

1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፤

2. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 20 በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፣

3. የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 እና አ/አበባ ለገሃር አመልድ ህንፃ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ 7ኛ ፎቅ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ።

4, የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ባህር ዳር ዋናው ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሣጥኑ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሸጎ 8፡30 ይከፈታል። የተጠቀሱት የመክፈቻ እና የመዝጊያ ቀናቶች የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በእለቱ ቀን 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል።

5. የጨረታው ውድድሩ በሎት/በምድብ ድምር ዋጋ የሚታይ ሲሆን በአንድ ሎት /ምድብ/ ለተጠየቁ የስራ ዝርዝሮች ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሞላት አለበት።

6. በጨረታ የተሞላወው ዋጋ የጨረታ ሠነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ45 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል።

7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር

ባህር ዳር-058-218-0538/ 09-18-01-06-17/ 09-18-71-66-16

አዲስ አበባ፡- ስልክ ቁጥር 011 126 5338/ 09-20-24-93-20/ 09-11-90-86-29

የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-18
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-18 14:30
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
  • Bid bond: የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 20 በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published: Jun 04, 2026
  • Posted at: 2026-06-04T07:32:19.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders