የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የሥራ ሰዓት የመግቢያና መውጫ መቆጣጠሪያ ሲስተም ከነማሽኑ፣ የርቨር ዩፒኤስ፣ ፕሪንተር እና ከለር ፕሪንተር ዕቃዎችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ውድድር ከአቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ኢሎአ/011/2018

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የሥራ ሰዓት የመግቢያና መውጫ መቆጣጠሪያ ሲስተም ከነማሽኑ፣ የርቨር ዩፒኤስ፣ ፕሪንተር እና ከለር ፕሪንተር ዕቃዎችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ውድድር ከአቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ሥራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ሎተረ አገልግሎት ስም በተከፈተ የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000004652782 ገቢ በማድረግ ዋናውን ማስረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

ተጫራቾች በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም የጨረታ ማስከበሪያ ብር 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ በማስያዝ ዋናውን ማስረጃ ከጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶችን የቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶችን የያዘ አንድ ዋና እና አንድ ቅጂ ለየብቻው በፖስታ በማድረግና በጽሑፍ በመለየት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ክሊራንስ፣ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስከር ወረቀት፣ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገባበት ቅፅ ሞልታችሁ ማህተምና ፊርማ አድርጋችሁ የመጫረቻ ሰነዶቻችሁን አሟልታችሁ በማቅረብና የጨረታ ማስከበሪያውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ እስከ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው።

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መ/ቤት ይከፈታል።

-አገልግሎቱ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታወን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-7816 ደውሎ መረዳት ይቻላል።

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-18
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-18 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት
  • Bid bond: 150,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 04, 2026
  • Posted at: 2026-06-04T07:47:04.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders