በኢትዮጵያ የንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ የመኪና ዕቃ መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የገዥው መለያ ቁጥር፦ ት/ልአ⁄ዘ ግዥ ብ/ግ/ጨ/03/2018

በኢትዮጵያ የንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ ከዚህ በታች ለተጠቀሱት የተለያዩ ፈጣን እንቅስቃሴ ያላቸው(veco, Tracker, lsuzu, Nisan and Eitcher, Toyota, Hyundai, Dongfong, Daewoo bus, Sunlong bus, ZNA rich pickup Kia Automobile Lifan Automoble and Addis Geely Automobile )የመኪና ዕቃ መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር የግዥ መስፈርቶቹን የሚያሟሉ እና በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት በጨረታው ላይ ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው።

  1. ተጫራቾች በዘርፋ ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም ጨረታው እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ ሊያገለግል የሚችል የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ ክሊራንስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን እነዚህ ሰነዶች በኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በማሸግና በመግለጽ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ሰነዶች ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያው ቀነ ገደብ በፊት ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለሚወዳደሩበት የመኪና ዕቃ መለዋወጫ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከግንቦት 26/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከሰአት ከ7፡30-11፡30 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ሰዓት ድረስ ግዥ ክፍል አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 17 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ። (አድራሻው ከስር ተገልጿል።)
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ሰኔ 16 ቀን 2018 ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ከላይ ለተጠቀሰው ፈጣን እንቅስቃሴ ያላቸው የመኪና ዕቃ መለዋወጫ ፡- ብር 100,000.00(አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዘርፍ ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው። ኢንሹራንስ ቦንድና ቼክ ተቀባይነት የላቸውም። ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲው ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።
  6. ተጫራቾች የቴክኒክ መወዳደሪያ የቴክኒክ ሰነድ እና የፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ በፖስታ በማሸግና ኮፒ እና ኦርጅናል የፋይናንሻል እንዲሁም የቴክኒካል ሰነድ ኮፒዎችን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ሁሉንም ፖስታዎች በማድረግ ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። አድራሻ ከታች ተገልጿል።
  7. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ መጠን 10 ፐርሰንት /አስር ፐርሰንት/ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ ስም አሰርተው ውሉን የሚፈጽሙ ይሆናል፡፡ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ እቃው በመነጋጋር ለአንድ አመት የሚቆይ ዉል በመዋዋል በዉሉ መሰረት የምንረካከብ ይሆናል።
  8. ዘርፉ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ የሀብት አስተዳደርና ግዥ ዋና ክፍል

አድራሻ፦ አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጠሳና ኮርኪ ፋብሪካ ፊት ለፊት ሸገር ህንፃ

አካባቢ አለ በጅምላ ግቢ ውስጥ ስልክ ቁጥር 011 455 2358 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-23
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-06-23 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Jun 04, 2026
  • Posted at: 2026-06-04T08:30:28.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders