የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 37/2018
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች የቤትና ቢሮ ዕቃዎች የተለያዩ የምግብ ነክ ዕቃዎች የመኪና እና የሞተር ሳይክል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች (ግለሰብም ሆነ ድርጅት) ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1, ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጨራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደስ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታዉን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ፣ ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ-6፡00 ሰዓት ድረስ በቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት (1000174515488) የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር) በማስገባት hawassaawegaged (ECCH-ዕቃ አወጋገድ ሥራ ሂደት 2018) በሚለው የቴሌግራም ግሩፕ ስሊፕ በመላክ የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይቻላል።
3. ያገለገለ ተሸከርካሪ/ሞተርሳይክል) ላይ መወዳደር የሚፈልግ ተጫራች ማንኛዉም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጲያዊ መወዳደር ይችላል።
4. ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም የተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላለ ዋጋ 5%(አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን C.P.O በማሰራት የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪ ሀራጅ ጨረታ ለሚሳተፉ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ የተገለጸው የጨረታ ዋስትና( C.P.O) መጠን ለእያንዳንዱ ኮድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው (በስድስተኛው) ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡05 ፔፕሲ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የሐዋሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት አዲሱ መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ተከፍቶ ጨረታው የሚጀምር ሲሆን ግልፅ ጨረታው ከተጠናቀቀ ከ10ደቂቃ በኃላ የሀራጅ ጨረታው ይጀመራል። ነገር ግን ጨረታው በበዓል እሁድ ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታ ይሆናል።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለዉ ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታ ከነ ቫቱ በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልክ በመሙላት በታሸገ እንቬሎፕ ወይም ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከዚህ ሰነድ ዉጭ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ለመቀበል አይገደድም።
7. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተስብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም። በተጨማሪ ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈተ በኃላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠዉን ዋጋ እና መግለጫ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም።
8. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታዉ ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ዉድድር ማግለል አይችልም። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።
10. ተጫራቾች የዕቃዉን ናሙና ሳያዩ ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም።
11. ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው።
12. አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5(አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል።
13. ቅ/ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡- 046-212-5396 / 046-212-6595
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-10
- Publishing entity: Hawassa Custom Commission Branch Bureau
- Bid bond: 5%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Jun 04, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.