ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ. ለህንፃ ግንባታ ሲጠቀምበት የነበረውን ቁርጥራጭ እንጨቶች እና ፕላይውድ (ሳፋሪያን) ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
(RefNo. TISC/HRPA/017/2026)
ኩባንያችን ለዋና መ/ቤት ህንፃ ግንባታ ሲጠቀምበት የነበረውን ቁርጥራጭ እንጨቶች እና ፕላይውድ (ሳፋሪያን) ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
- ለመሸጥ የተዘጋጁትን ቁርጥራጭ እንጨቶች እና ፕላይውድ (ሳፋሪያን)ፒያሳ አዲስ አበባ ሬስቶራንት ፊት ለፊት በሚገኘው የኩባንያው ህንፃ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት ተከታታይ ሰባት ቀናት በአካል በመገኘት እና በማየት የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የቀድሞው ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ዋና መ/ቤት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ በማድረግ መጫረት ይችላሉ።
- ጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት ተከታታይ ሰባት ቀናት ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በስምተኛው ቀን ጠዋት 4፡30 ተጫራቾች በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት ተከታታይ ሰባት ቀን ድረስ ቦሌ ከሚገኘው የኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 106 በአካል በመገኘት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- በሌሎች ተጫራቾች በተሰጠ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ወይም ተመስርቶ ዋጋ ማቅረብ በጥብቅየተከለከለ ነው።
- የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% በተጨማሪነት ይከፍላሉ።
- የጨረታው አሸናፊዎች ውጤት ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያውን በመፈፀም ንብረቱን ከቦታው ሙሉ በሙሉ ማንሳት ይኖርባቸዋል።
በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክፍያ የማይፈጽሙ አሸናፊዎች ያስያዙት CPO ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111119771/70/0968580008 በመደወል ወይም ከላይ በተጠቀሰው ዋና መ/ቤት በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል።
ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ.
Tender details
- Deadline: 2026-06-11
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት ተከታታይ ሰባት ቀናት
- Bid opening: 2026-06-12 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በስምተኛው ቀን ጠዋት 4፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tsehay Insurance S.C.
- Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
- Published: Jun 05, 2026
- Posted at: 2026-06-05T07:08:03.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.